1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጤፍ አዋዛጋቢነትና ናጎያ ፣

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 3 2005

ባለፈው ሳምንት በዚህ ክፍለ ጊዜ ፣ እንዳወሳነው ፣ በዓለም ውስጥ ፣ ኢትዮጵያ ብቻ የተገኘውና ለብዙ ሺ ዓመታት ፤ በኢትዮጵያ አርሶ አደሮች እየለማ ተጠብቆ የኖረው፤ ጤፍ ፣ በአሁኑ ዘመን ፤ ከኢትዮጵያ ተወስዶ በሌሎች አገሮች እየተዘራ ጥቅም በመስጠት

https://p.dw.com/p/170oN
ምስል Helge Bendl

ላይ ይገኛል። ጤፍ ፤ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ፤ ለምግብነት ያለው ጠቀሜታ ይበልጥ ታዋቂነት እያስገኘለት ነው። ጤፍንና የእርሱ ተዛማጅ የሆኑትን የእህል ዓይነቶች ማሽላ፣ ዳጉሣንና የመሳሰሉትን እንዲህ ተፈላጊ ያደረጋቸው ምን እንደሆነ ባለፈው ሳምንት ዶ/ር መላኩ ወረደ ከጀመሩልን በመቀጠል እንዲህ ያብራራሉ።

24112006 PZ TEFF.jpg
ምስል DW-TV

አሁን እንዳዳመጣችሁት፤ ጤፍ በውስጡ ከሚገኙ አካል ጠጋኝ ማዕድናትና ቪታሚን (ቪታሚን D 6 ) ሌላ ተመራጭ ያደረገው ፣ በገብስ፤ ስንዴና አጃ በመሳሰሉ እህሎች ዱቄቱ ፤ ሲቦካ ፤ ሊጡ እንደ ላስቲክ እንዲሳብ የሚያደርገው የፕሮቲን ቅልቅል የሆነው Gluten የተባለው ንጥረ ነገር የሌለበት በመሆኑ ነው ። ታዲያ ፤ «ግሉተን» ያለባቸውን ምግቦች አንጀታቸው ለማይቀበል፣ ለሚጠናወታቸው ሰዎች፣ ጤፍ ተስማሚነቱ አያጠራጥርም። ከጤፍ ጋር ተያይዞ ፣ «ከግሉተን ነጻ የሆነ ምግብ» የሚባለው ዘይቤ በዚህ በምዕራቡ ዓለም የተለመደ ሆኗል።

የጤፍን ሰብልነት ፤ የጤፍን ጠቀሜታ፣ ማነው ዘመናት ሙሉ ጠብቆ ለዓለም ያስተዋወቀው? ውርጭ፤ ተባይ በቀላሉ የማያጠቃው ምን ዓይነት ባህርይ ቢኖረው ነው?

ከኢትዮጵያ ጋር ፣ ጤፍን በጋራ ለመጠቀም በሚል ስምምነት ከኢትዮጵያ ጋር ተዋውሎ ከሠርሁ በማለት፤ ለኢትዮጵያ አርሶ አደሮች አንዳች ጠቀሜታ ያልሰጠው Crop and Soil (HPFI) የተሰኘው የኔደርላንድ ኩባንያ፤ ባለፈው ዝግጅት እንደጠቀስነው፤ ሌላ ስም ያላቸው ሌሎች ኩባንያዎች አቋቁሞ፣ ኩባንያው፤ በአውሮፓ የጤፍ ዱቄትን ከሌሎች አዝርእት ዱቄት ጋር ቀላቅሎ የተለያዩ የምግብ ዓይነት የሚያቀርብበት ሰፋ ያለ የባለቤትነት መብት ያለው መሆኑን በአውሮፓ አስመዝግቦ ይህን ራሱ ላቋቋማቸውሌሎች ኩባንያዎች አሳልፎ ሰጥቷል። ኩባንያው በጀርመን ሀገርም ተባባሪዎች አሉት። ጤፍ፣ በታህታይ ሳክሰኒ (ኒደርሳኽሰን)ተዘርቶ መብቀልና ማፍራት መቻሉም ታውቋል።

Europäisches Patentamt Logo
የአዉሮጳ የግኝት ባለቤትነት ሰጪ ጽ/ቤት ዓርማ

ጀርመን ውስጥ በልዩ የምግብ ሱቆች፤ የተፈጥሮ ባህርያቸው በሰው ሠራሽ መንገድ ካልተለወጠም ሆነ ካልተቀየጠ አዝርእት የሚዘጋጁ የምግብ ዓይነቶችና ዱቄት በሚሸጥባቸው ንዑሳን መደብሮች፤ የጤፍ ዱቄት በውድ ዋጋ ነው የሚሸጠው፤ 100 ግራም በአንድ ዩውሮ ገደማ ነው የሚሸጠው። ከሠርሁ ባለው ኩባንያም ሆነ ሌላ ስም በተሰጣቸው ኩባንያዎች ባለቤትነት የሚሠራጨው ታሽጎ የሚሸጠው ጤፍ መሆኑ ነው። ባለፈው ሳምንት በጨረፍታ እንደጠቀስነው፤ ኢትዮጵያ ጥንቃቄ ካላደረገች፤ ወደፊት አርሶ አደሮቿ ጤፍ ለመዝራት የውጭ ኩባንያ ፈቃድ የሚጠይቁበት ሁኔታ ሊከሠት ይችል ይሆናል። እንደ ቴክኒካዊ ግኝቶች የተፈጥሮ ውጤቶችን እዚህም ላይ ለምሳሌ አዝርእትን ፤ የግል ባለንብረት አድርጎ ለማስመዝገብ የሚደረገው ሙከራ ፣ እዚህ አውሮፓ ውስጥ ዋና ጽ/ቤቱ በሙዩኒክ (ሙዑንሸን) የሚገኘውን የፈጠራ ውጤት ወይም ግኝት ማስመዝገቢያ ጽ/ቤት (European Patent Office)ጭምር ማለት ነው አላሳሰበም አይባልም። «ባዮ ፓቴንት» እጅግ አነጋጋሪና አሳሳቢም ጉዳይ ነው። ለማንኛውም፣ የራስን ንብረት መጠበቅ እንጂ ፣ በማንኛውም መልኩ ለሌላ አሳልፎ መስጠት ኀላፊነት ከሚሰማው ከየትኛውም ወገን አይጠበቅም።

BdT Erntezeit in Grossenhain
ምስል AP

ኢትዮጵያ፤ የጤፍን ዘር ለዓለም ያስተዋወቀች ሆና ሳለ፤ ጠብቀው ያቆዩት አርሶ አደሮቿ

ሳይጠቀሙ ሌሎች ብልጣ ብልጥ ባዕዳን ኩባንያዎች ለመቆጣጠር የሚያደርጉት ሙከራ

በቂ ማስጠንቀቂያ ይመስለናል። ሃገራት የተፈጥሮ ሃብታቸውን የአዝርእት ባለቤትነታቸው ታውቆ እንዲከበር የናጎያ ስምምነት ናጎያ ፕሮቶኮል ምን ዓይነት ዋስትና የሚሰጥ ነው? ኢትዮጵያ በዚህ ስምምነት ተሳትፎዋ ምን ይመስላል? የብዝሃ ህይወት ንብረትን በመጠበቅ ረገድስ ከዜጎች ምንድን ነው የሚጠበቀው? በግብርና ሚንስቴር የብዝሃ ህይወት ጥበቃ ተቋም (ኢንስቲቱት) ዋና ሥራ መሪ(ዳይሬክተር ) ዶ/ር ገመዲ ዳሌ ---

ተክሌ የኋላ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ