1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች ዉለታ

ሐሙስ፣ የካቲት 19 2007
https://p.dw.com/p/1EiGg

«እኛ ሃገር ባህላዊ ሆነዉ እየተከበሩ ያሉት በዓላት የሐይማኖት በዓላት ናቸዉ። የሐይማኖት በዓላት እድሜ ለአባቶቻችን እና ለእናቶቻችን ከባህላችን ጋር በደንብ አድርገዉ እንደ ጥሩ ስፊት እንደ ጥሩ ስንደዶ ማንም በማያላቅቀዉ ሁኔታ ሰፍተዋቸዋል ባህላዊም ሆነዋል ። የካቲት 12 እኮ ዳቦ አይቆረስለት፤ ቡና አይፈላለት፤ በግ አይታደርለት፤ ጠላ አይጠመቅለት፤ ጉዝጓዝ አይጎዘጎዝለት እንዴት አድርጎ ከባህላችን ጋር ሊዋሐድ ይችላል? የአዋሃደዉም ሰዉ የለ» ሲሉ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የዛሬይቱ ኢትዮጵያን ስላቆዩን ስለ ጥንት አባቶቻችን እና እናቶቻችን የድል ቀናት አከባበርና ታሪክ እየተረሳ መምጣት በተመለከተ አስተያየታቸዉን ሰጥተዉናል። በዛሬዉ ዝግጅታችን የአባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ያበረከቱት አስተዋፅዖ በታሪክ ብቻ ተፅፎ የሚቀመጥ ሳይሆን፤ ህያዉ ሆኖ እንዲኖር ታሪካችንን ማስተማር ለትዉልድ ማስተላለፍ አለብን፤ የሚሉንን እንግዶች አስተያየት አቀናብረን ይዘናል።