1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጸጥታው ምክር ቤት የበረራ እገዳ በሊቢያ ላይ

ዓርብ፣ መጋቢት 9 2003

ሲጠበቅ የነበረው ውሳኔ ትላንት ጸደቀ። በሊቢያ ሰማይ አውሮፕላን ዝር አይልም።

https://p.dw.com/p/RAe7
ምስል dapd

የሊቢያ ሁኔታ እንደመሰንበቻው አስክፊ እንደሆነ ቀጥሏል። የኮነሬል ሞአመር ጋዳፊ ኃይሎች አማጺያኑ የተቆጣጠሩዋቸውን ከተሞች ከሰማይና ከምድር መቀጥቀጥ፤ የሰው ህይወት ማጥፋታቸውን አላቋረጡም። ሲያወዛግብ የነበረውና የጋዳፊ ኃይሎችን ግስጋሴ ሊገታ ይችላል ተብሎ የተገመተው የበረራ እገዳ ውሳኔ ትላንት ምሽት ጸድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ታዟል። የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ለቀናት ላይ ታች ሲልና ሲሟገትበት ቆይቶ አሁን ከውሳኔ ደርሷል። የበረራ እገዳን ጨምሮ ሌሎች ማዕቀቦችን በጋዳፊ ላይ ጥሏል። 10 ሀገራት የደገፉትና አምስቱ ድምጸ ታዕቅቦ ያደረጉበት ውሳኔ በእርግጥ አማጺያኑን አስፈንድቋል። ውሳኔውን በተመለከተ አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዘገባ አለው።

አበበ ፈለቀ

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሀመድ