1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፀሐይ ግርጃ በእስያ፣

ረቡዕ፣ ሐምሌ 15 2001

በእስያ፣ በሁለቱ ታላላቅ አገሮች ፣ በህዝብ ብዛትም በዓለም ውስጥ አንደኛና ሁለተኛ በሆኑት ቻይናና ህንድ ፣ የዚህ ምዕተ ዓመት ዋንኛ የተባለው የፀሐይ ግርጃ ዛሬ ጎህ ሲቀድ ጀምሮ ታይቷል።

https://p.dw.com/p/IvNS
የፀሐይ ግርጃ በእስያ፣
ምስል picture-alliance/ dpa

250 ኪሎሜትር ገደማ ስፋት ባለው ቦታ ከህንድ፣ በቻይና በኩል እስከጃፓንና ምዕራባዊው ሰላማዊ ውቅያኖስ የዘለቀው ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ለ 6 ደቂቃ ከ 39 ሴኮንድ የተጋረደችበት የተፈጥሮ ትርዒት መታየት የጀመረው፣ በህንድ፣ ጎህ ሲቀድ ፣ ከሌሊቱ ፣ ከ 5 ሰዓት ከ 28 ደቂቃ ጀምሮ(እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ፣ 11 ሰዓት ከ 28 ደቂቃ ላይ)ነው።

ይህን የተፈጥሮ ትርዒት በብዛት ህዝብ ሲያየው ያሁኑ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዘመናዊ ሥነ-ቴክኒክ በመገሥገሥ ላይ በሚገኙትና ጥንታዊ ባህል ባላቸው በሁለቱ አገሮች ፣ ሳይንስና ባህላዊ አመለካከትም ሆነ እምነት መጋጨታቸውንም ለመታዘብ ተችሏል። በጉጉት፣ ትርዓቱን ለማየት ከመነሣሣት አንስቶ በፍርሃት መዋጥ ፣ ሁኔታውን መጥፎ ገድ አድርጎ የመመልከቱ ሁኔታም የተዛመተ መሆኑ የታወቀ ነው።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ