1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፀረ ባህር ላይ ዉንብድና ተልዕኮ

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 2 2001

በሶማሊያ የባህር ግዛት በአደን ባህረ ሰላጤና አካባቢዉ የሚታየዉ ዉንብድና በርካታ አገራትን መነካካቱን ተከትሎ ፀረ የባህር ላይ ዉንብድና ርምጃ ለመዉሰድ አነሳስቷል።

https://p.dw.com/p/GDpZ
የተያዙ ወንበዴዎች በኬንያ ችሎት
የተያዙ ወንበዴዎች በኬንያ ችሎትምስል picture-alliance/ dpa
በዚሁ መሰረትም የአዉሮጳዉ ኅብረት ባቀደዉ ተልዕኮ ዉስጥ የጦር ኃይሏ እንዲሳተፍ የጀርመን ካቢኔ ትናንት በሙሉ ድምፅ ወስኗል። የምክር ቤቱን ዉሳኔና ለተልዕኮዉ የሚሰጠዉን የስልጣን ገደብ ገና ቢሆንም። የባህር ላይ ወንበዴዎቹ መፈልፈያ ባህሩ ሳይሆን የብሱ ነዉና ምንጩን ማድረቅ ይገባል የሚሉ ወገኖች የእርታ እህል የጫኑ መርከቦችን እያጀቡ ማሳለፉ ብቻ መፍትሄ ተደርጎ መወሰድ እንደሌለበት ይናገራሉ።