1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳዩ ጥቃት አድራሽ መታሠር

ሰኞ፣ መጋቢት 12 2008

ባለፈዉ ኅዳር ወር በፓሪስ የ130 ሰዎችን ሕይወት ለቀጠፈዉ እና በርካቶችን ላቆሰለዉ ያሸባሪዎች ጥቃት ዋና ተፈላጊ የነበረዉ ሳላህ አብደስላም ዓርብ ዕለት ብራስልስ ዉስጥ መገኘት ብዙዎችን አስገርሟል።

https://p.dw.com/p/1IH8Y
Salah Abdeslam Fahndungsfoto
ምስል Police Federale Belgien

ግለሰቡ ብራስልስ ዉስጥ ተሸሽጎ በርካቶችን የሃሳቡ ተባባሪ ማድረጉ ስለተገመተ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን እና አባሪተባባሪዎችን ለመያዝና የአሸባሪዎችን መረብ ለማግኘት ከብራስልስ ዉጭ በሌሎች የአዉሮጳ ከተሞችም ክትትል እየተደረገ ነዉ። ተጠርጣሪዉ ከብራስልስ መኪና በመከራየት እና በሾፌርነት የፓሪሱን ጥቃት እንዳቀነባበረ ወይም በዋናነት እንደተሳተፈም ይገለፃል። ጥቃቱ እንደተፈጸመ ማምሻዉን ወደ ቤልጂየም መግባቱ ተረጋግጦ ነበር። ግን ደግሞ ላለፉት አራት ወራት ምንም ፍንጭ ስላልተገኘ ምናልባት ወደሶርያ ሳይሻገር እንዳልቀረ ተገምቶ ነበር። እሱ ግን እዛዉ ብራስልስ ከፖሊሶች ብዙም ሳይርቅ መክረሙ ተሰምቷል። ገበያዉ ንጉሤ ዝርዝሩን ከብራስልስ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ