1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፈረንሳይና ጣሊያን ዉዝግብ በሼንጌን

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 19 2003

አራተኛው የዜና መጽሄት ርዕሳችንም ትኩረቱ በጣልያንና ፈረንሳይ ላይ ነው። የሼንጌን ቪዛ የያዘ ሰው፤ በሼንጌኑ ውል መሰረት በአባል ሀገራት ያለቪዛ መንቀሳቀስ ይችላል። ሰሞኑን ግን ጣሊያን ቪዛ ሰጥታ ወደ ፈረንሳይ የሰደደቻቸውን ስደተኞች ፈረንሳይ ከድንበር ላይ አቁማ በመጡበት እግራቸው መልሳቸዋለች።

https://p.dw.com/p/RKgC
የፈረንሳይና የጣሊያን መሪዎችለውይይት
የፈረንሳይና የጣሊያን መሪዎች ለውይይትምስል picture-alliance/dpa

ሁኔታው በፈረንሳይና ጣሊያን መካከል እሰጥ-አገባ ፈጥሮ ቆይቷል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጉዳዩ ላይ ተገናኝተው ቢወያዩም ለጊዜው ግን ከስምምነት ላይ አልደረሰሱም። ለመሆኑ የሼንጌን ስምምነት ምንድን ነው? ዓላማውስ ምን ይመስላል? ተክሌ የኌላ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴን ከጥቂት ሠዓታት በፊት አነጋግሮት ነበር። ገበያው የሼንጌን ውል ታሪካዊ ዳራን ባጭሩ በማስቀመጥ ይጀምራል።

ገበያው ንጉሴን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተክሌ የኋላ