1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፊፋ አዲስ ፕሬዝዳንት ምርጫ ና ማሻሻያዎች

ዓርብ፣ የካቲት 18 2008

የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ደቡብ አፍሪቃዊው እጩ ራሳቸውን ከምርጫው በማግለላቸው ለፊፋ ፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት አራት እጩዎች ብቻ ነበሩ ።

https://p.dw.com/p/1I37H
Schweiz Zürich FIFA Außerordentlicher Kongress Stimmenzahl
ምስል Reuters/R. Sprich

[No title]

ዓለም ዓቀፉ የእግር ኳስ ፌደሬሽን ፊፋ የቀድሞውን ፕሬዝዳንት ሴፕ ብላተርን ለመተካት ዛሬ ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር ምርጫ የስዊሱ ጊያኒ አንፋንቲኖ አብላጫ ድምፅ ቢያገኙም ለማሸነፍ የሚያበቃቸውን ሁለት ሶስተኛ ድምፅ አላሟሉም ። የመጀመሪያው ዙር ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ደቡብ አፍሪቃዊው እጩ ራሳቸውን ከምርጫው በማግለላቸው ለፊፋ ፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት አራት እጩዎች ብቻ ነበሩ ። ፊፋ ከምርጫው በፊት ባካሄደው ጉባኤ መጠነ ሰፊ የውስጥ አሰራር ማሻሻያዎችን አጽድቋል ። እነዚህ ማሻሻያዎችም በሚቀጥሉት 60 ቀናት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚሆኑ ተገልጿል ። አዲሱ የፊፋ ፕሬዝዳንት የድርጅቱን ገፅታ የመቀየር ከባድ ሃላፊነት ይጠብቃቸዋል ። ስለ አዲሱ የፊፋ ፕሬዝዳንት ምርጫ የስፖርት ጋዜጠኛ ኢብራሂም ሻፊን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ