1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 5 2009

በኢትዮጵያ የፋሲካ በዓል የፊታችን እሁድ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ይከበራል። የእምነቱ ተከታዮች ከእንሰሳት ተዋጽኦዎች ራሳቸውን የሚቆጥቡበት ጾም ማብቂያ ሲቃረብ ለአቀባበሉ ዝግጅት ማድረግ አለ። ከነዚህም አንዱ ለበዓል የሚያስፈልጉ ምግቦች ሸመታ ነው ።

https://p.dw.com/p/2bDAN
Äthiopien Market in Mekele
ምስል DW/Y. G. Egziabher

Market for Easter Holiday - MP3-Stereo

ለመሆኑ የበዓል ገበያ እንዴት ነው ?ስለ ስኳር፣ ቡና፣ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ዶሮ፣ በግ እና ሌሎችም የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ምን የታዘቡትን ያጋሩን አሉ። በአዲስ አበባ ቄራ አከባቢ እንደምትኖርና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ መሆኗን የምትናገረው ራሄል ክፍሌ የፆም ፍች ስለሆነ ምግብ መስራት እንደሚጠበቅባት ትናገራለች። የሸቀጦቹ ዋጋ ቢጨምርም፣ ነጋዴዎቹም ዋጋ የመቀነስ አዝማምያ ባያሳዩም፣ ህዝቡ ለመሸመት ወዲያ ወዲህ እያለ እንደሆነም ራሄል ትናገራለች። ፆም ሲገባ ሰላጣና ቲማቲም እንደምወደድ ሁሉ የፆም መፍቻ በዓል በመጣ ቁጥር የየምግብ ሸቀጦች ላይም እንደምጨምርም ራሄል ትናገራለች።

የአዲስ አበባ ነዋር መሆናቸዉን የሚናገሩት አቶ አበበ ብሰጥ የተባሉት ግለሰብ የዶሮና የበግ ዋጋ «ከምነግርህ» በላይ በመወደዱ «ስጋን ማሽተት እንጅ መብላት የሚቻልበት ዘመን አይደልም» ስሉም ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። መቼም ሁለት ወር ተጹሞ ሳይበሉ ከመቅረት ዉድም ቢሆን ሰዉ ኢየገዛ እንደሆነም ይናገራሉ።

አሁን የሚከበረዉ የፋሲካ በዓል ለየት የሚያደርገዉ የመንግስት ሠራተኞች ደሞዝ ጭማሪ ከተደረገ እና ነጋዴዎች በምግብ ሽቀጦች ላይ ዋጋ ከጨመሩ በኋላ የሚከበር በዓል መሆኑን ነው።

በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ደህረገጽ ላይ የምግብ ሽቀጦች ወጋ መናር በመለከተ አስተያየታቸውን ያጋሩን አሉ። አለሙ ደረበዉ የተሰኘ የፌስቡክ ስም ያላቸው ግለሰብ ተከታዩን ብለዋል፣ «አኛሰ ችግርም የለብን ከዘይት በሰተቀር፣ ከሰክዋር ከበሬ ሰጋ መወደድ ፣ ከበግ ና ከፍየል ሙክት ዋጋ መናር በቀር ፣ እኛማ ምን ጎደሎን ። አረ ምን ቸግሮን ምን ጠፍቶ ወተት ና የወተት ተዋፅኦ ተረት ተረት ሆኖ ፣ ቅቤ መብላት በአያቶቻችን ቀንተን ፣ ክብረ በአላትን መጡልን ሳይሆን መጣብን ሰንል ፈርተን ፣ ለሽንኩርቱ ለበርበሬው ዋጋ ተሳቀን፣ አረ ምን ችግር አለብን ?

ሌላ መስፍን ጌታቸዉ  የተባሉት ደግሞ «ስኳር ዘይት ምናምን ያው ሰልፈኛው ህዝባችን ትዕግስቱ እስኪንጠፈጠፍ ተሰልፏል !!! አገኘም አጣ ሰልፍ የኑሮው መገለጫ ሆንዋል!!! ሲነጋ ሰልፍ!!! ለታክሲ ሰልፍ ! ለነዳጅ ሰልፍ! ለኤቲዬም ሰልፍ!!!» ስሉ አስተያየታቸዉን አጋርቶናል።

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ