1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፋይናንስ ቀዉስ መፍትሄ አሰሳ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 8 2001

ቀዉስ ዉስጥ የገቡት አገራት ጀርመንን ጨምሮ በየደረጃዉ የየራሳቸዉን መፍትሄ እየሞከሩ ነዉ።

https://p.dw.com/p/GHx9
ጀርመን ያቅሟን እያለች ነዉ
ጀርመን ያቅሟን እያለች ነዉምስል AP

የምዕራቡን ዓለም የመታዉን የፊናንስ ቀዉስ ተከትሎ የተከሰተዉ የምጣኔ ሃብት ድቀት ገና ብዙ ሊቆይ ይችላል የሚል ስጋት በማስነሳቱ ብዙዎችን አሳስቧል። በተለይ ደግሞ ዓለም ከመቼዉም ይበልጥ አሁን የመተሳሰሯ ነገር እንዱን የመታዉ ቀዉስ ሌላኛዉን ከሚያምንበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ችግሩ ሁሉንም ነካክቷል። መገናኛ ብዙሃኑ በየምክር ቤቱ በዚሁ ዙሪያ የሚደረገዉን ዉይይትና የመፍትሄ አሰሳ ድርድር በየዕለቱ መዘገባቸዉ የወቅቱ ከፍተኛ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል። ሰዎችም ከሸቀጥ ዋጋ መናር አንስቶ በየደረጃ ሳያነሱት የማያልፉት ርዕስ የምጣኔ ሃብትና የፋይናንስ ቀዉስ ከሆነ ሰነባብቷል።