1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ ግንቦት 23 2009

በኢትዮጵያ የሚገኙ አገር አቀፍ ፖለትካ ፓርትዎች ከገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ጋር ለመደራደር ዉይይት ከጀመሩ ከሶስት ወር በላይ አስቆጥረዋል።

https://p.dw.com/p/2dvLW
Karte Äthiopien englisch

Code of Conduct for Political parites Negotiaion Observers - MP3-Stereo

በዚህም ግዜ ዉስጥ ብዙ ውይይቶችን አድርገዋል። ዉይይቱን ሲጀመር 22 ፓርቲዎች ቢጀምሩም እስካሁን የዘለቁት ድርድሩ ከመካከላቸው በተመረጡ አደራዳሪዎች እንዲመራ የተስማሙት 17 ፓርቲዎች ናቸው። መድረክና ሰማያዊ ፓርቲ፣ ገለልተኛ የሆነ ሶስተኛ አካል ያዳራድረን የሚል አቋም ይዘው ራሳቸዉን ከዉይይቱ አግለዋል።
ከትናንት በስተያ 17ቱ ፓርቲዎች ድርድሩን ለሚታዘቡት የስነ-ምግባር ደንብ ማፅደቃቸዉን የዉይይቱ ተሳታፍዎች ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ስለ ሥነ-ምግባር ደንቡ ይዘት አስተያየታቸውን ከሰጡን መካከል የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትን ወክለው በዉይይቱ ላይ የተሳተፉት የፓርቲዉ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉጌታ አበበ አንዱ ናቸው።

በቀጠዩ ስብሰባ ታዛቢዎች ባሉበት የድርድር አጃንዳዎች እንደሚጸድቁና ድርድሩም በይፋ እንደሚጀመር ተዘግቧል። የኢትዮጵያ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ ለድርድር ስለ ሚቀርቡት አጀንዳዎች ለዶቼቬለ ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።

የመድረክና፣ የሰማያዊ ፓርት አመራርን ጨምሮ ሌሎች የፖለትካ ተንታኞች ገለልተኛ የሆነ ሶስተኛ አካል ድርድሩን ካልመራ ድርድሩ ዉጤት እንደማይኖረዉ ይናገራሉ። ገዢዉ ፓርቲ ኢህአዴግም ድርድሩን በአገሪቱ ለተፈጠረዉ የፖለቲካ ቀዉስ ጊዜ መግዣነት እየተጠቀመበት ነው ሲሉም የሚተቹና የድርድሩን ሕደት ታዓማንነት በጥርጣሬ የሚመለከቱም አልጠፉም።

በቀጣይ የድርድር አጀንዳዎችን ለማጽደቅ በሚደረገው ዉይይት ከ106 በላይ ተሳታፍዎች ይገኛሉ ስልም የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ