1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬስ ነፃነት ሚና ለዲሞክራሲ ግንባታ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 23 2006

የግል መገናኛ ብዙሃንና የመንግሥት ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጋዜጠኞች መንግሥትና ህብረተሰቡ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ። ምሁራንም በተለያዩ መንገዶች የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል ።

https://p.dw.com/p/1Bs6Y
Zeitungen Äthiopien
ምስል DW

በአንድ አገር ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ መገናኛ ብዙሃን የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ የመስኩ ባለሞያዎች አስታወቁ ። ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ የነፃ ፕሬስ ሚና በዲሞክራሲያዊ ህብረተሰብ ግንባታ በሚል ርዕስ በተካሄደው ውይይት ላያ የተሳተፉ የግል መገናኛ ብዙሃንና የመንግሥት ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ጋዜጠኞች መንግሥትና ህብረተሰቡ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ። ምሁራንም በተለያዩ መንገዶች የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከፍ በማድረግ የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል ። ቪዥን ኢትዮጵያ ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ የተባለው ድርጅት ባካሄደው በዚሁ ስብሰባ ላይ ከ60 በላይ የግል ሚዲያና የመንግስት ጋዜጠኞች መካፈላቸውን አዘጋጁ አስታውቀዋል ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ