1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዝደንት ኦባማ ጉብኝት መልዕክትና ፋይዳዉ

እሑድ፣ ሐምሌ 26 2007

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ በምስራቅ አፍሪቃ እና በአፍሪቃ ቀንድ ያደረጉትን ጉብኝት አጠናቀዉ ወደመደበኛ ተግባራቸዉ ተመልሰዋል።

https://p.dw.com/p/1G891
Äthiopien Addis Abeba Obama Rede Afrikanische Union
ምስል Reuters/J. Ernst

የፕሬዝደንት ኦባማ መልዕክት ፋይዳዉ

የእሳቸዉ የኬንያ እና ኢትዮጵያ ጉብኝትም ሆነ በጉብኝታቸዉ ወቅት ያደረጓቸዉ ንግግሮች ግን አሁንም የበርካቶች መነጋገሪያ እንደሆኑ ነዉ። ፕሬዝደንት ኦባማ ገና ለጉብኝት እግራቸዉን ሳያነሱ ሃሳባቸዉን እንዲለዉጡ ከመጠየቅ ጀምሮ፤ የሰብዓዊ መብት ይዛታ እና የመገናኛ ብዙሃን ነፃነት ያሳስበናል ያሉ የመብት ተሟጋቾችም የሁለቱን ሃገራት መሪዎች ሲያገኙ ሊያነሷቸዉ ይገባል ያሏቸዉን ነጥቦች በደብዳቤ ከትበዉ አድርሰዋቸዋል። ፕሬዝደንቱ ግን ባመዛኙ የጉብኝታቸዉ ዋና ዓላማ በሆኑ ጉዳዮች ተጠምደዉ ታይተዋል። ሳምንታዊዉ እንወያይ የጉብኝታቸዉን ፋይዳና መልዕክት ዳስሷል። ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ይከታተሉ።

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ