1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዝዳት ኦባማ ጉብኝትና ንግግር በበርሊን

ረቡዕ፣ ሰኔ 12 2005

ኦባማ በንግግራቸዉ የሰዉ ልጅ እኩልነት፥ የመንቀሳቀስና የመሥራት መብቱ እንዲከበር፥ የኩሌር ጦር መሳሪያ ቅነሳ እንዲደረግ ጠይቀዋል።አስተናጋጃቸዉ የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክልም የዲሞክራሲ ሥርዓትና የሕዝብ ነፃነትን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል

https://p.dw.com/p/18tBW
U.S. President Barack Obama waves after giving a speech in front of the Brandenburg Gate in Berlin June 19, 2013. Obama's first presidential visit to Berlin comes nearly 50 years to the day after John F. Kennedy landed in a divided Berlin at the height of the Cold War and told encircled westerners in the city "Ich bin ein Berliner", a powerful signal that America would stand by them. REUTERS/MichaelKappeler/Pool (GERMANY - Tags: POLITICS )
ምስል Reuters


ጀርመንን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ዛሬ ከጀርመንዋ ርዕሠ-ከተማ በርሊን ብራንደርቡርግ ቶር ከተሰኘዉ ታሪካዊ ሥፍራ ለመላዉ ዓለም ንግግር አድርገዋል።ኦባማ በንግግራቸዉ የሰዉ ልጅ እኩልነት፥ የመንቀሳቀስና የመሥራት መብቱ እንዲከበር፥ የኩሌር ጦር መሳሪያ ቅነሳ እንዲደረግ ጠይቀዋል።አስተናጋጃቸዉ የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት ወይዘሮ አንጌላ ሜርክልም የዲሞክራሲ ሥርዓትና የሕዝብ ነፃነትን ማክበር አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።ሁለቱ መሪዎች ባደባባይ ንግግር ከማድረጋቸዉ በፊት የተለያዩ ዓለም አቀፉ ጉዳዮችን አንስተዉ ተወያይተዋል።ንግግርና ዉይይቱን የተከታተለዉን የበርሊኑ ወኪላችንን ይልማ ሐይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።-------

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ዛሬ በበርሊን የአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አደረጉ። ፕሬዝደንት ከሆኑ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጀርመንን የጎበኙት ኦባማ ከፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ እና ከመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጋ ሀሳብ ተለዋውጠዋል። ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም የአገራቸዉ የስለላ ተቋም የመገናኛ ዘዴዎች ላይ ባካሄደዉ ክትትል ከ50 ያላነሱ አደጋዎች ከሽፈዋል፤ ሕይወትም ተርፏል ብለዋል። አገራቸዉ ሶርያ ዉስጥ ለመዋጋት ተዘጋጅታለች የሚለዉ የተጋነነ አስተሳሰብ መሆኑን በማመልከት የቡድን ስምንት አባል መንግስታት የሶርያን ቀዉስ በድርድር ለመፍታት መስማማታቸዉን አድንቀዋል። ሆኖም አሜሪካ ለሶርያ አማፅያን ስለምትሰጠዉ የድጋፍ ዓይነት ከመግለፅ ተቆጥበዋል። ኦባማ
ከጀርመን መሪዎችም ጋ በአዉሮጳ ኅብረትና በአሜሪካ መካከል ከቀረጥ ነጻ ንግድ ስለማካሄድም ተወያይተዋል።
«ከመራሂተ መንግስት ሜርክል እና ቀደም ሲልም ከፕሬዝደንታችሁ ጋ ባደረግነዉ ዉይይት በእኛ በኩል ከአዉሮጳ ጋ የሚኖረን ግንኙነት የነፃነታችንና የደህንነታችን የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን አስታዉሻቸዋለሁ፤ አዉሮጳ በምናደርገዉ ነገር ሁሉ ተጓዳኛችን ነዉ፤ እናም ምንም እንኳ የሚገጥሙን ተግዳሮቶች ቢለያዩም የፅናታችን ትስስርና የምንጋራቸዉ ሃሳቦች በጋራ እሴቶቻችን ላይ የተመረኮዙና ዘላቂ ናቸዉ።»
ሜርክል በበኩላቸዉ በዉይይቱና በደረሱበት የጋራ መግባባት መደሰታቸዉን ገልጸዉ ለተግባራዊነቱ ጀርመን ተግታ እንደምትሰራ አመልክተዋል። ከባለቤታቸዉና ከልጆቻቸዉ ጋ ወደበርሊን የመጡት ኦባማ ከቀትር በኋላ 4000 የተጋበዙ እንግዶች በተገኙበት በበርሊኑ ብራንደር-ቡርገር ቱር ተገኝተዉ ንግግር አድርገዋል። በዚሁ ንግግራቸው የሀገራቸውን የኑክልየር ጦር መሣርያ በአንድ ሦስተኛ ለመቀነስ ቃል ገብተዋል፤ ሌሎች የኑክልየር ኃይላት ይህንኑ የጦር መሣርያ ዓይነት እንዲቀንሱ ጥሪ አቅርበዋል። ፕሬዝደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በዚሁ ስፍራ እኔም የበርሊን ኗሪ ነኝ ሲሉ ታሪካዊ ንግግር ካደረጉ ዘንድሮ በያዝነዉ ወር 50 ዓመት ሆነዉ።

German Chancellor Angela Merkel shakes hands with U.S. President Barack Obama after their speeches next to Berlin Mayor Klaus Wowereit (R) at the Brandenburg Gate in Berlin, June 19, 2013. U.S. President Barack Obama will unveil plans for a sharp reduction in nuclear warheads in a landmark speech at the Brandenburg Gate on Wednesday that comes 50 years after John F. Kennedy declared "Ich bin ein Berliner" in a defiant Cold War address. REUTERS/Tobias Schwarz (GERMANY - Tags: POLITICS)
ምስል Reuters

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ