1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ቀዉስ በየመን

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 27 2006

በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የየመን መንግሥት ተቃዋሚዎች፤ መንግሥት መልስ እስኪሰጠን በተቃዎሞአችን እንቀጥላለን ሲሉ በመዲናይቱ ሰንዓ ጎዳናዎች መዉጣታቸዉ ተነገረ።

https://p.dw.com/p/1D5SL
Jemen/ Demonstration/ Sanaa
ምስል Reuters

ተቃዋሚዎቹ የሀገሪቱን ፓርላማ መግቢያ ጎዳናም አጥረዉ ይዘዉ መዉጫና መገበያያንም መዝጋታቸዉ ነዉ የተነገረዉ። ሰልፈኞቹ በጥያቄያቸዉ እነሱን የማይወክለዉ የጠቅላይ ሚንስትር የመሀመድ ባዚንዳዋ መንግሥት ከስልጣን ተወግዶ፤ በምትኩ አንድ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ መንግሥት እንዲቋቋም ጠይቀዋል። ይህ ወዴት እንደሚያመራ የማይታወቀዉ የየመን ዉስጣዊ ዉዝግብ የተመድን እና የአዉሮጳን መንግሥታት እያሳሰበ መጥቶዋል። የዶይቸ ቬለዋ ኬርስትን ክኒፕ ስለየመን የፖለቲካ ቀዉስ ያጠናቀረችዉን ዘገባ ይልማ ኃይለሚካኤል እንዲህ ያቀርበዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ