1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ ተ መ ድ 5ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ዘገባ

ረቡዕ፣ መስከረም 29 2006

ከ 318 ዓመታት በፊት ፣ እ ጎ አ በ 1705 ዓ ም መሆኑ ነው፣ ታላቁ እንግሊዛዊ የፊዚክስ ና የሒሳብ ሊቅ አይዛክ ኒውተን፤ ስለ ስበት ኃይልና ስለብርሃን ምንነት ካደረገው ምርምር ውጭ ፣ ስለ ኅልፈተ ዓለም በማንሳት፤ እ ጎ አ በ 2060 ዓ ም፣

https://p.dw.com/p/19x3Q
ምስል Sudipto Das

ሊያጋጥም ይችላል ሲል በማስታወሻው ላይ ማሥፈሩየሚጠቀስ ነው። መንግሥታት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ካልወሰዱ ፣ ትንበያው በአርግጥ የማይፈጸምበት ምክንያት አይኖርም። ያለፈው ሰሞን ማስጠንቀቂያም፣ ጎርጎሪዮሳዊው 2100 ከመድረሱ በፊት ለጥፋት የሚዳርግ አደጋ ተጋርጧል ነው ያለው።

Klimakonferenz Valencia Greenpeace Aktion
ምስል AP

በአሁኑ ዘመን ፣ የዓለም ሕዝብ ቁጥር 7 ቢሊዮን መድረሱ ከታወቀ ወዲህም ቢሆን፣ በፍጥነት እየጨመረ በመኼድ ላይ መሆኑ እሙን ነው። የህዝብ ቁጥር መጨመር ደግሞ በፕላኔታችን ላይ ከባድ ጫና ማሳረፉ የሚያጠራጥር አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ የሰዎች ጥንቃቄ የጎደለው እርምጃ፣ምድራችንን ለጥፋት የሚዳርግ ብርቱ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚያስከትል፣ ከመስከረም 13-16, 2006 ፤ በአስቶክሆልም እስዊድን የተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በይነ መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ነክ ም/ቤት፤ በአንግሊዝኛው አሕጽሮት (IPCC) ማስገንዘቡ የሚታወስ ነው። የምድራችን ግለት እጨመረ መኼድ፤ በሰሜንና በደቡብ የምድር ዋልታ አካባቢ በተለያዩ ደሴቶችና በባህር ጠረፎች፤ ሊያጋጥም ስለሚችለው አደጋ በአየር ንብረት ላይ ያተኮሩ የሳይንስ ጠበብት 5ኛውን ዘገባይፋ ባደረጉበት ሰነድ ላይ ሳያስገነዝቡ አላለፉም።

በሌሎች የዓለም ክፍሎች፤ እዚህም ላይ በሰሜን ምሥራቃዊው አፍሪቃ ወይም በኢትዮጵያ ፣ በዚህ ረገድ ምንድን ነው የሚያሠጋው አደጋ? አደጋውንስ ለመቋቋም ምንድን ነው መደረግ ያለበት? የ 110 ሃገራት ተወካዮች በተገኙበት የአስቶክሆልሙ ጉባዔ ኢትዮጵያን ወክለው በዚያ የተሳተፉትን የአየር ንብረት ጉዳይ ባለሙያ አነጋግረናል ።

Klimawandel Wüste Sandfeld Gilf Kebir
ምስል picture-alliance/ dpa

በቅርቡ በአስቶክሆልም በተካሄደው ጉባዔ፣ የአየር ንብረት ተመራማሪዎች ፣ ለዓለም መንግሥታት ያቀረቡት የጥናት ውጤት ዋና መልእክትም ሆነ ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው?

በኢትዮጵያ ብሔራዊ የአየር ጠባይ ጥናት ድርጅት(ኤጀንሲ) የአየር ጠባይ(ሚቲዮሮሎጂ) ትንበያና ማስጠንቀቂያ የሥራ አመራር ዋና ኀላፊ(ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር) አቶ ድሪባ ቆሪቻ--

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ