1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ «ፊፋ» ቀውስና የጀርመን እግር ኳስ ፌደሬሽን

ሰኞ፣ ግንቦት 24 2007

የዓለም የእግር ኳስ ፌደሬሽን፤ በሙስና ሲታማ አዲስ ነገር አይደለም። ይሁንና ባለፈው ሳምንት ፌደሬሽኑ በዋናው ማዕከል በዙሪኽ፤ እስዊትስዘርላንድ የሁለት ቀናት ዐቢይ ጉባዔ ሊያካሂድ በዝግጅት ላይ እንዳለ በዋዜማው ፤ በጉቦ ተጠርጥረው 7 የፌደሬሽኑ ሠራተኞች የተያዙበት ሁኔታ ፤ አስደንጋጭነቱም ፣ አስገራሚነቱም ፤ በሰፊው አነጋግሯል።

https://p.dw.com/p/1FaIu
ምስል picture-alliance/dpa/M.Tirl dpa/lhe

[No title]

ዩናይትድ ስቴትስም 14 ሰዎች በፍርድ ቤት እንዲመረመሩ ማዘዛ ማውጣቷ ተነግሯል። ይህ ሁሉ ሲሆን ፤ የFIFA ፕሬዚዳንት የሰፍ ብላተር ከ 17 ዓመት የሥልጣን ዘመን በኋላ እንደገና ለ 4 ዓመት በመረጣቸውም ፤ ከጀርመን የእግር ኳስ ፌደሬሽን (DFB) ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ ነው ሂደቱን የተከታተለው። ይህን በተመለከተ የበርሊኑን ዘጋቢአችንን ይልማ ኃ/ሚካኤልን በስልክ አነግሬዋለሁ።

ተክሌ የኋላ

ይልማ ኃ/ሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ