1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ 7 ኪሎ መጽሔት ምረቃ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 30 2008

በፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ኪነ-ጥበባዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት እንደሚያደርግ የተነገረው 7ኪሎ የተባለ መጽሔት ሰሞኑን በዩናይትድ ስቴትስ ሲልቨርሰፕሪንግ ሜሪላንድ ግዛት ተመርቋል።

https://p.dw.com/p/1H3Iw
USA Äthiopische Zeitschrift 7 kilo
ምስል DW/N. Debebe Wolde

[No title]

መጽሔቱ የተመሰረተው በሶስት የቀድሞ አዲስ ነገር ጋዜጣ አዘጋጆች ጋዜጠኞች አማካኝነት ነው። በምረቃ ሥነ- ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፣ የመጽሔቱ መስራቾች ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በሪፖርተርነትና አርታኢነት በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ ሲሰሩ ቆይተዋል። በስደት የሚገኙት ጋዜጠኞች በሰሜን አሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የጀመሩት 7 ኪሎ የተባለው መጽሔት በየሁለት ወሩ የሚታተም ይሆናል። 7ኪሎ በኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሀል ምን ተጽእኖ ይፈጥር ይሆን?

ናትናኤል ወልዴ

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ