የ DV( የቪዛ ሎተሪ) ማመልከቻ፣
ዓርብ፣ መስከረም 23 2007ማስታወቂያ
ከ 40 ዓመት በፊት ኢትዮጵውያን ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ውጭ ፣ በተለይም ወደ ምዕራባውያን ሃገራት ወጥተው ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ትውልድ አገራቸው መመለስ ብቻ ነበረ የሚታያቸው። እ ጎ አ በ 1961 እና 1970 መካከል ብቻ ፣ ለምሳሌ ያህል በዩናይትድ ስቴትስ፣ 2 ሰዎች ብቻ ነበሩ የፖለቲካ ተገን የጠየቁ። ከዚያ ወዲህ ሁኔታው እጅግ መለዋወጣቸው የታወቀ ነው። በ 4 ዐሠርተ ዓመታት ውስጥ ያን የቆየ ሁሉም ነገር በትውልድ ሀገር የሚል አቋምንም ሆነ አመለካከትን ያስለወጡ፣ ከትውልድ ሀገር የበለጠ የውጭ የሚያስመኙ ምክንያቶች ለመፈጠራቸው የብዙ ወጣቶችና ጎልማሶች አዝማሚያ ሳይጠቁም አይቀርም። በተለያዩ ምክንያቶች በመፍለስ፤ በመሰደድ አገር ለቀው የሚውጡ ኢትዮጵያውን ቁጥር እጅግ ብዙ ነው። የ DV ሁኔታ ደግሞ ትንሽ የተለየ ነው። ለማንኛውም፣ የአዲስ አበባው ዘጋቢአችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ለቀጣዩ ዘመን የ DV ማመልከቻ ያስገቡ ሰዎችን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ