1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ G7 ጉባኤ ጀመረ

እሑድ፣ ግንቦት 30 2007

ቡድን ሰባት በመባል የሚጠሩት ሰባቱ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት አገራት መንግሥታትና የመንግሥታት ተጠሪዎች በጀርመን ባቫርያ ግዛት በሚገኘዉ ታዋቂዉ «ኤልማዉ» ጥንታዊ ቤተ መንግሥት ዉስጥ ጉባኤያቸዉን ጀመሩ።

https://p.dw.com/p/1Fd35
G7 Gipfel Elmau Merkel und Obama Konferenz
ምስል Getty Images/AFP/A. Jocard

የጀርመን የዩኤስ አሜሪካ፤ የካናዳ፤ የፈረንሳይ፣ የጃፓን፣ የኢጣልያ እና የብሪታንያ ፖሊተከኞች የሚካፈሉበት ይህ የሁለት ቀን ጉባኤ በተለይ በከባቢ አየር ጉዳይ ለማስጠበቅ አሸባሪነትን ለመዋጋት እንዲሁም በዓለም የንግድ ጉዳይ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል። ጉባኤዉ ከመጀመሩ በፊት የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የዩኤስ አሜሪካዉን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ተቀብለዉ አነጋግረዋል። ሁለቱም መሪዎች የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት አስፈላጊነት አስመርዉበታል። በሌላ በኩል ይህንን ጉባኤ በመቃወም ጉባኤዉ በሚካሄድበት አቅራቢያ በሚገኝ አነስተኛ ከተማ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ተካሂዶአል። እንደ ብዙኃም መገናኛዎች ዘገባ ይህን ጉባኤ ደህንነት ለማስጠበቅ ወደ 20 ፀጥታ አስከባሪዎች ተሰማርተዋል፤ ወደ 3000 ሺህ የሚሆኑ ጋዜጠኞች ደግሞ ለዘገባ ቦታዉ ላይ ይገኛሉ።

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ