1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ16ተኛው ዓ/ዓቀፍ የኤች አይ ቪ ኤድስ እና የአባለዘር በሽታዎች ጉባኤ ፍፃሜ

ዓርብ፣ ኅዳር 29 2004

ካለፈው እሁድ አንስቶ አዲስ አበባ ውስጥ ሲካሄድ የቆየው ዓለም ዓቀፍ የ ኤች አይ ቪ ኤድስ እና የአባለዘር በሽታዎች ጉባኤ ዛሬ አብቅቷል ።

https://p.dw.com/p/S0tQ
ምስል DW

ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተሳታፊዎችን ባስተናገደው በዚሁ ጉባኤ ላይ በርካታ የምርምር ፅሁፎች ቀርበው ውይይቶችም ተካሂደዋል ። ለ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና ህክምና ከለጋሽ ሃገራት የሚገኘው ገንዘብ እየቀነሰ የመሄዱ ስጋት የጉባኤው አንዱና ዋነኛ የመነጋገሪያ ርዕስ ነበር ። ከሰራ በታች በሚገኘው የአፍሪቃ ክፍል ብቻ 22.9 ሚሊዮን ሰዎች ከ ኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር በሚኖርባት በአፍሪቃ ለኤድስ መድኃኒት እና ህክምና የሚያስፈልገው ገንዘብ እጅግ ከፍተኛ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ለችግሩ ብልሃት ማፈላለጉ አብይ ትኩረት ተሰጥቶታል ። ጉባኤው ስለተነጋገረባቸው ጉዳዮች ሂደቱን ሲከታተል የቆየውን የአዲስ አበባውን ወኪላችንን ታደሰ እንግዳውን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ታደሰ እንግዳው

ሂሩት መለሰ