1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ19 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስከሬኖች ተገኙ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 11 2008

በዕለተ ሐሙስ ኮንጎ ከዛምቢያ በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ የጸጥታ ኃይሎች ለድንገተኛ ፍተሻ ባስቆሙት ተሽከርካሪ ውስጥ ከአስከሬኖቹ በተጨማሪ 76 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህይወት መገኘታቸውን የዜና አውታሩ ጨምሮ ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1J9K5
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የኮንጎ የድንበር ጠባቂዎች በኦክስጅን እጥረት የሞቱ 19 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስከሬኖችን በደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ ማግኘታቸውን ባለስልጣናት ዛሬ አስታወቁ። የኢትዮጵያውያኑ አስከሬኖች የተገኙት « የማጥወልወል ስሜት» የሚፈጥር ሽታ በቀሰቀሰው ጥርጣሬ መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። በዕለተ ሐሙስ ኮንጎ ከዛምቢያ በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ የጸጥታ ኃይሎች ለድንገተኛ ፍተሻ ባስቆሙት ተሽከርካሪ ውስጥ ከአስከሬኖቹ በተጨማሪ 76 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በህይወት መገኘታቸውን የዜና አውታሩ ጨምሮ ዘግቧል። የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አካባቢያዊ ድንበር ጠባቂ ኃላፊ ዦን ፕየር ሉቦሻ ስደተኞቹ የተሻለ ህይወት ፍለጋ በኬንያ ወደ ደቡብ አፍሪቃ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ ተናግረዋል ብለዋል። በህይወት ያሉት ስደተኞች እና አስከሬኖቹ ለዛምቢያ ባለስልጣናት መሰጠታቸውን ጨምረው ገልጠዋል።

እሸቴ በቀለ

ኂሩት መለሰ