1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2004 አበይት ክንዉኖች

ሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2004

ነሐሴ አስራ-አራት ሩቅ አሳቢዉ ቅርብ አደሩ።ጠቅላይ ሚንስት መለስ ዜናዊ አረፉ።በአስራ-ሰወስተኛዉ ቀን ተቀበሩ።ነሐሴ-ሃያ ሰባት።መለስ ኮንትራት ካሉት የአምስት አመት ዘመነ-ሥልጣን ቀሪዉን የሚፈፅሙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/166Lh
***Für mögliche Ergänzungen der Karte, wie z.B. andere Sprachen, zusätzliche Orte oder Markierungskreuz, wenden Sie sich bitte an infografik@dw-world.de (-2566), Außerhalb der Bürozeiten an bilder@dw-world.de (-2555).*** DW-Grafik: Per Sander 2011_03_10_Laender_Prio_A_B

በሁለት ሺሕ አራት በስተመጨረሻዉ ዛሬ-ከአዲስ አበባና ከናይሮቢ የሰማነዉ የእስረኞች መለቀቅ፥ የይቅርታ፥ድርድር ዜና የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ሒደት የመቀየሩ ተስፋ መሆን አለመሆኑ ነገ-አንድ በሚለዉ አዲስ ዓመት ሒደት የሚታይ ነዉ።ዜናዉ ግን ከእስራት፥ ዉንጀላ፥ ከግጭት፥ ቁርቁስ፥ ከታታላቅ ኢትዮጵያዉያን ሞት ሌላ ምንም ወይም በጣም ጥቂት በጎ ነገር ለተሰማበት ለነገዉ አሮጌ ዓመት በርግጥ የምሥራች ብጤ ነዉ።የሁለት ሺሕ አራት የኢትዮጵያ አበይት ክንዉኖች ደግሞ የዛሬ ርዕሳችን።ላፍታ አብራችሁን ቆዩ።


የቀድሞዉ የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጥቅምት።ጠቅላይ ሚንስትሩ የጋዜጠኝነትና የአሸባሪነትን ልዩነት፥ የነጭና የጥቁር ደም ቀለምን አንድነት፥ ለተነተኑበት ማብራሪያ ምክንያትና ከሆነዉ አንዱ ሁለት የሲዊድን ጋዜጠኞች ያለ ሕጋዊ ፍቃድ ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ መያዛቸዉ ነበር።

ዛሬ ካዲስ አበባ እንደተሰማዉ እኒያ ሁለት ጋዜጠኞች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል።ከሁለቱ ጋዜጠኞች ጋርም አንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ የሚሆኑ እስረኞች በይቅርታ።ይለቀቃሉ።

የዛሬዉ አሮጌ ዓመት ሁለት ሺሕ አራት ሊብት ሁለት ወር ሲቀረዉ ሰኔ የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦነግን)፥ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ)፥ የግንቦት ሰባት ለለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲን ከአል-ቃኢዳና አሸባብ ጋር ደብሎ በአሸባሪነት ፈረጃቸዉ።

ሐምሌ ግም ሲል ኋላ የተዘጋዉ የአዉራምባ ጋዜጣ አዘጋጅ ዉብሸት ታዬና አሁን በመዘጋትና አለመዘጋት መሐል የተንጠለጠለዉ የፍትሕ ጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ በሁለት ቀን ልዩነት ታስረዉ በአሸሪነት ተከሰሱ።ሁለቱ ጋዜጠኞች ኋላ የበርካታ ዓመታት እስራትና የገንዘብ መቀጮ ተበይኖባቸዋል።ወንጀሉ ያዉ አሸባሪነት ነዉ።

ወዲያዉ ሲዊድናዊ ፎቶ ግራፍ አንሺ ጆን ፔርሰንና ዘጋቢ ማርቲን ሺብዬ ከኦብነግ ታጣቂዎች ጋር ሆነዉ ከሶማሊያ የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠዉ ሊገቡ ሲሉ መያዛቸዉ ተሰማ።ታሕሳስ ላይ ከአሸባሪዎች ጋር በማበር ወንጀል እያንዳዳቸዉ አስራ-አንድ አመት እስራት ተበየነባቸዉ።

የሁለቱ የዉጪ ጋዜጠኞች መታሰር የኢትዮጵያዉያኑን ጋዜጠኞችና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የመታሰር፥ መወንጀል፥ መሰደድን ዜና በጀቦነበት በሁለት ሺሕ አራት ዋዜማ የተቃዋሚዎቹ የኦሮሞ ፌደራሊስትና የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ አባላት አቶ በቀለ ገርባ እና አቶ ኦልባና ሌሌሳ ታሰሩ።ከዕለታት በሕዋላ አርቲስት ደበበ እሸቱም ወሕኒ ተወረወረ።ወንጀላቸዉ፥ መንግሥት እንደሚለዉ የአሸባሪ ድርጅት አባላት ወይም ተባባሪዎች ናቸዉ።

ያም ሆኖ ያዉ ያመት ግብር፥ ወግ፥ ባሕል ነዉና ሐበሻ ከአዲስ አበባ እስከ ሳንሆዜ አዲስ ዓመት አለ።ሁለት ሺሕ አራት።ከበጎ ተስፋ፥ ከጥሩ ምኞት፥ ከመልካም ፀሎት ጋር እዮሐ አበባዬ።

ኢዮአበባዬዉ፥ ተዘፍኖ፥ ምኞት ተስፋዉ ተነግሮ፥ ፀሎት ምልጃዉ ሳያበቃ የተቃዋሚዉ የለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ አንዱአለም አራጌና ታዋቂዉ የፖለቲከ ሐያሲና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በርካታ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ታሰሩ።

ሁለት ሺሕ አራት ገና አራተኛ ቀኑ ነበር።ዓለም አቀፉ የሠብአዊና የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በኢትዮጵያ መንግሥት እርምጃ ላይ ዉግዘት፥ተቃዉሟቸዉን ያዥጎደጉዱት ያዙ።ተቃዋሚ ፖለቲከኞችም እንዲሁ።ደበበን ከመፍታት በስተቀር የሰማቸዉ ግን አልነበረም።

እንዲያዉም ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ጥቅምት ላይ ለምክር ቤታቸዉ በሰጡት ማብራሪያ የመንግሥታቸዉን እርምጃ ተገቢነት አረጋገጡ።

ትናንት በርግጥ ዛሬ አይደለም።ዛሬ ከናይሮቢ የድርድር ጅምር ተዘግቧል።የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ከወነጀለዉ ሁለቱን ጋዜጠኞች አስርጎ አስገብቷል፥ ጋዜጠኞቹ በተያዙበት ወቅት አምስት ታጣቂዎቹ ተገድለዉበታል፥ ካለዉ ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር ኦብነግ ጋር ናይሮቢ ዉስጥ ሥለ ድርድር ለመደራደር አንድ ሁለት ማለቱ ተረጋግጧል።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ።የኦብነግ የዉጪ ግንኙነት የኢትዮጵያ ጉዳይ ሐላፊ አቶ ሐሰን አብዱላሒ የሰጡት ምክንያት ለየት ይላል።ግን ድርድሩ እዉነት ነዉ።



ነገ-ሌላ ቀን ነዉ።ጊዜዉ ይሮጣል።ሁለት ሺሕ አራት በሲዊድን ጋዜጠኞች ብይን፥ በእነ አንዱዓለም አራጌ የፍርድ ቤት ዉጣዉረድ ታሕሳስን አሰናብቶ ጥርን ሲቀበል፥ አዲስ አበባ አስራ-ስምተኛዉን የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ለማስተናገድ ሽር ጉድ ማለት ጀምራ ነበር።ከወደ ሰሜን ግን መርዶ ተሰማ።ጥር ዘጠኝ።

አርታ ዓሌ የተሰኘዉን የአፋር መስተዳድር ይገበኙ ከነበሩ አዉሮጳዉያን መካከል አምስቱ በታጣቂዎች ተገደሉ።ሌሎች ታገቱ።የታገቱት ከብዙ ዉጣ ዉረድ፥ ከወራት በሕዋላ ተለቀቁ።የአጋች-ታጋቾቹ ድራማ ግን የኢትዮጵያና የኤርትራን የቆየ የቂም ቁርሾ ቁስል ሳያመረቅዝ አልተዘጋም ነበር።

ኢትዮጵያ ሐገር ጎብኚዎቹን ያገቱትንና ሌሎችንም የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሐይላት ታስታጥቃለች፥ ፥ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤን ለማሸበር አሲራ ነበር ያለቻትን ኤርትራን ለመቅጣት ጦር አዝምታ የኤርትራን ወታደራዊ ተቋማት ደበደበች።


አቶ ሽመልስ ከማል የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ።መጋቢት ነበር።ጥር በተደረገዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ አንድ ያለዉ ትልቅ ጉባኤ በሁለት ሺሕ አራት አዲስ አበባን በጉባኤ አንበሻብሿታል።አስራ-ሰወስተኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ፥ የዓለም የምጣኔ ሐብት ጉባኤ፥ የኢጋድ ጉባኤ፥ የሱዳኖች ጉዳይ ጉባኤ፥ የሶማሊያ ጉዳይ ጉባኤ እና ሰኔ እንደገና የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ።

የሰኔዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ለኢትዮጵያ የመጥፎ ምልኪ አማጭ መስሏል።ሐምሌ ሁለት ሺሕ ሰወስት የተጀመረዉ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሐይማኖታዊ ጥያቄ እስከ መጋቢት የዉይይት ድርድር መልክና ባሕሪ አልተለየዉም ነበር።የሙስሊሞቹ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ሊቀመንበር አቡበከር አሕመድ።መጋቢት።


ድርድሩ በጠብ ተቀይሮ መጀሪያ አሳሳ አርሲ ዉስጥ ሕይወት አጠፋ።አዲስ አበባ ሰኔ ላይ ለሁለተኛዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ስትሰዘጋጅ ደግሞ የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች የአወሊያ መስጊድን ወርረዉ በርካታ ሙስሊሞችን ደበደቡ፥ አሰሩ፥ አጋዙም።መንግሥት የሰጠዉ ምክንያት ያዉ አሸባሪ የሚል ነዉ።ከራሱ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ይደራደሩ የነበሩት የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም ተለቃቅመዉ ታሰሩ።

የሰኔዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ ሰኞ ሊጀመር አርብ ማታ የኢትዮጵያ ወታደሮች መስጊድ ለመዉረር ከመዝመታቸዉ በፊት አርብ ቀን ላይ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት አንዱዓለም አራጌና እስክንድር ነጋን ጨምሮ በአሸባሪነት በተወነጀሉት ሃያ አራት ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች ላይ ከሰባት አመት እስከ እድሜ ልክ የሚደርስ ቅጣት በየነ።


ታደሰ እንግዳዉ።ይሕ ዘገባ በአዲስ አበባ ለዶቼ ቬለዉ ዘገቢ ለታደሰ እንግዳዉ የመጨረሻዉም ሆነ። ቀልጣፋዉ፥ ፈጣኑ፥ በሳሉ ጋዜጠኛ እሁድ በመኪና አደጋ ሞተ።ሰላሳ-ዘጠኝ አመቱ ነበር።

የሞት ነገር ከተነሳ፥ ታዋቂዉ ደራሲ፥ ጋዜጠኛና ሐያሲ ስብሐት ገብረ እግዚአብሔር የሞተዉ ዘንድሮ ነዉ። የካቲት።ሥነ-ፅሑፍ አድናቂ፥ አክባሪዉ በሥብሐት ሞት ሲያዝን ሲተክዝ የኢትዮጵያ መንግሥት ሥኳር ለማምረት በሚል ለሸንኮራ ተክል የከለለዉ ሰፋፊ ግዛት ከአፋር አርብቶ አደሮች፥ እስከ ዋልድባ ገዳም መነኮሳት መጉዳቱ የቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ተባብሶ ቀጥሎ ነበር።

የዋልድባ ገዳም የወደፊት እጣ ፈንታ ሲያከራክር ከሃያ ዓመት በላይ የተከፋፈሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የሐይማኖት አባቶች ከመወጋገዝ ወደ ድርድር ያዘነበሉት ዘንድሮ ነበር።ሲያትል ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በስማ በለዉ የተጀመረዉ ድርድር የካቲት አጋማሽ ወደ ፊትለፊት ዉይይት ከፍ ብሎ ነበር።


ንግስት ሠልፉ።የድርድሩ መቀጠል አለመቀጠል ሲያነጋግር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ ፓትሪያርክ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ በትንሽ ቀናት ሕመም አረፉ።ሰባ ስድስት አመታቸዉ ነበር።ቀብራቸዉ።ነሐሴም ተጋመሰ።የሞት ነገር ካነሳን እዉቁ የሥ’ነ-ሥዕል ጠቢብ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ የሞቱትም ዘንድሮ ነዉ። ሚያዚያ።ሰማንያ ዓመታቸዉ ነበር።

እሳቸዉ ደግሞ አመቱ መባቻ ላይ እንዳሉት በርግጥ ሩቅ አስበዉ፥ አልመዉም ነበር።

ነሐሴ አስራ-አራት ሩቅ አሳቢዉ ቅርብ አደሩ።ጠቅላይ ሚንስት መለስ ዜናዊ አረፉ።በአስራ-ሰወስተኛዉ ቀን ተቀበሩ።ነሐሴ-ሃያ ሰባት።መለስ ኮንትራት ካሉት የአምስት አመት ዘመነ-ሥልጣን ቀሪዉን የሚፈፅሙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ናቸዉ።


ነጋሽ መሐመድ

Begräbnis des Patriarchen der äthiopisch-orthodoxen Kirche, Abune Paulos *** Autor/Copyright: Getachew Tedla/DW, 23.08.2012
ቀብር አቡነ ጳዉሎስምስል DW
The flag-draped casket of Ethiopia's Prime Minister Meles Zenawi is seen during his funeral ceremony in the capital Addis Ababa, September 2, 2012. Meles, praised for economic reform but criticised for authoritarianism during his 21-year rule of one the world's poorest countries, died overnight on August 20 in a Brussels hospital after a long battle with illness. He will be buried in a state funeral in Addis Ababa today. REUTERS/Tiksa Negeri (ETHIOPIA - Tags: POLITICS OBITUARY)
ቀብር- አቶ መለስ ዜናዊምስል REUTERS
Ethiopian state television announced on August 21, 2012 that Hailemariam Desalegn will be acting prime minister, after the death of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi.
የወደፊቱ ጠቅላይ ሚንስትርምስል CC-BY-SA- World Economic Forum
epa03307749 (FILE) A file photo dated 17 September 2011 shows Ephiopian Prime Minister Meles Zeinawi speaking during a join press conference with his Egyptian counterpart Essam Sharaf (not pictured), in Cairo, Egypt. Reports on 16 July 2012 state that Meles Zenawi was unable to attend the opening on 15 July of the African Union Summit being held in Ethiopia because of rumoured health concerns. The Ethiopian government declined to make a statement on the issue. EPA/KHALED ELFIQI /POOL *** Local Caption *** 50045673
የቀድሞዉ ጠቅላይ ሚንስትርምስል picture-alliance/dpa

ሒሩት መለስ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ