1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ2007 ዓም የኢትዮጵያ ምርጫ ውጤትና አንድምታው

እሑድ፣ ሰኔ 21 2007

በዚህ ምርጫ ኢህአዲግ ና አጋር የሚላቸው ድርጅቶች ሁሉንም ወንበሮች ጠቅለለው መያዛቸው ፣ ውጤቱ አስቀድሞም የታወቀ ነው ሲሉ ለነበሩት ተቃዋሚዎችም ሆነ ሂደቱን ሲተቹ ለነበሩ ወገኖች አስገራሚ ሆኖ አልተገኘም ።

https://p.dw.com/p/1FoDE
Äthiopien Parlamentswahlen
ምስል DW/Y. G. Egziabhare

የ2007 ዓም የኢትዮጵያ ምርጫ ውጤትና አንድምታው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይፋ ያደረገው የ2007 ዓም ምርጫ የመጨረሻው ውጤት እንደሚያሳየው ገዥው ፓርቲ ኢህአዲግና አጋር ድርጅቶቹ 547ቱንም የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች አሸንፈዋል ። በአሁኑ ምርጫ ኢህአዲግ ባለፉት 5 ዓመታት በአንድ ተቃዋሚና በአንድ የግል ፖለቲከኛ ተይዘው የነበሩትን ሁለት መቀመጫዎችንም ወስዷል ። አንድም ተቃዋሚ የምክር ቤት መቀመጫ ያላገኘበት ፣ግንቦት 16፣2007 ዓም የተካሄደው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ፣የተለያዩ አስተያየቶችን እያሰነዘረ ነው ። በዚህ ምርጫ ኢህአዲግ ና አጋር የሚላቸው ድርጅቶች ሁሉንም ወንበሮች ጠቅለለው መያዛቸው ፣ ውጤቱ አስቀድሞም የታወቀ ነው ሲሉ ለነበሩት ተቃዋሚዎችም ሆነ ሂደቱን ሲተቹ ለነበሩ ወገኖች አስገራሚ ሆኖ አልተገኘም ። ምርጫው ፍትሃዊ ነፃም ሆነ ሰላማዊ እንዳልነበረ ሲናገሩ የቆዩት ተቃዋሚዎች የህዝብ ድምጽ በኃይል ተቀምቶበታል ያሉትን ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል ። ገዥው ፓርቲ ደግሞ የኢህአድግ ድል በሃገሪቱ የተመዘገበው የኤኮኖሚ እድገትና ዴሞክራሲ ውጤት ነው ሲል ይከራከራል ። የ2007 ዓም ብሔራዊ ምርጫ የመጨረሻው ውጤት ና አንድምታው የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ