1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ5ኛው አጠቃላይ ምርጫ የመጨረሻ ውጤት

ሰኞ፣ ሰኔ 15 2007

ገዥው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢ ሕ አ ዴ ግ እና አጋር ድርጅቶቹ ባለፈው ግንቦት የተካሄደው 5ኛው አጠቃላይ ምርጫ አሸናፊ መሆናቸውን የመጨረሻውን ይፋ ውጤት ዛሬ ይፋ ያደረገው ብሔራዊው የምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/1FloM
Äthiopien Wahlen EPRDF
ምስል DW/Y. G/egziabherZ

[No title]

ኢ ሕ አ ዴ ግ እና አጋር ድርጅቶቹ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያሉትን፣ 547 መንበሮች በጠቅላላ፣ ላለፉት አምስት ዓመታት በተቃዋሚ ፓርቲ አባል ተይዞ የነበረውን አንድ መቀመጫ ጭምር ማሸነፋቸውን የምርጫ ቦርዱ ኃላፊ ፕሮፌሰር መርጋ በቀና ይፋ አድርገዋል። ከዚህ ቀደም በግል ተወዳድረው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንበር አግኘተው የነበሩት የግል ፖለቲከኛ በተወዳደሩበት በቦንጋ ምርጫ አካባቢም ገዢው ፓርቲ ቀንቶታል። ኢ ሕ አ ዴ ግ ቢያሸንፍም ድምፁን ለመስጠት የወጣው መራጭ ቁጥር ከፍተኛ ነበር የተባለበት ምርጫ ጠንካራ ፉክክር የታየበት እንደነበር ፕሮፌሰር መርጋ ውጤቱን ይፋ ባደረጉበት ጊዜ አስታውቀዋል። ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን የአፍሪቃ ህብረት ታዛቢ ቡድን ቢያስታውቅም፣ የተቃዋሚ ወገኖች መንግሥት ምርጫውን ለማሸነፍ ሲል አምባገነናዊ ስልት ተጠቅሞዋል ሲሉ ወቀሳ አሰምተዋል።

አርያም ተክሌ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ