1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የAMISOM ተልዕኮ መራዘምና ዉዝግቡ

ሐሙስ፣ ግንቦት 20 2001

አንዳድ የሶማሊያ ጉዳይ የፖለቲካ ተንታኞችም ሠራዊቱ ሶማሊያ ዉስጥ መስፈሩ የሶማሊያን ግጭት-ዉዝግብ ከማስወገድ ይልቅ ይበልጥ እያባበሰዉ ነዉ ይላሉ

https://p.dw.com/p/HzZj
ደፈጣ ተዋጊዎችምስል AP

ሶማሊያ የሠፈረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ሠላም አስከባሪ ሠራዊት (AMISOM-በእንግሊዝና ምሕፃሩ) እዚያ የሚቆይበት ጊዜ መራዘሙ ድጋፍ፥ ተቃዉሞ፥ ዉግዘትም አስከትሏል።የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈዉ ማክሰኞ የሠራዊቱን ተልዕኮ በሥምንት ወራት አራዝሟል።ተልዕኮዉ መራዘሙን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፥የአፍሪቃ ሕብረትና የሶማሊያ የሽግግር መንግሥት ሲደግፉት የሶማሊያ ደፈጣ ተዋጊዎች አዉግዘዉታል።አንዳንድ የሶማሊያ ጉዳይ የፖለቲካ ተንታኞችም ሠራዊቱ ሶማሊያ ዉስጥ መስፈሩ የሶማሊያን ግጭት-ዉዝግብ ከማስወገድ ይልቅ ይበልጥ እያባበሰዉ ነዉ ይላሉ። ወኪላችን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲ ሲ ዝር ዝር ዘገባ አልኮልናል።

አበበ ፈለቀ/ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

►◄