1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የCPJ ዓመታዊ ዘገባ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2008

ቱርክ፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ደግሞ ከአራት እስከ ሥድስት ያለዉን ደረጃ ይጋራሉ።ድርጅቱ እንደሚለዉ እስከ ጎርጎሮሳዊዉ ታሕሳስ 1፤ 2015 ድረስ አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ጋዜጠኞች ሙያዊ ሐላፊነታቸዉን ለመወጣት በመሞከራቸዉ ብቻ በየሐገሩ ታስረዋል።

https://p.dw.com/p/1HNjQ
ምስል APTN

[No title]

የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ጋዜጠኞችን በማሠር በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ሥድስት መንግሥታት አንዱ መሆኑን ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ኮሚቴ ዘገበ። በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ CPJ ተብሎ የሚጠራዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት እንደዘገበዉ በርካታ ጋዜጠኞች በማሰር ቻይና፤ ግብፅ እና ኢራን የመጀመሪያዉን ሠወስት ሥፍራ ይዘዋል። ቱርክ፤ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ደግሞ ከአራት እስከ ሥድስት ያለዉን ደረጃ ይጋራሉ። ድርጅቱ እንደሚለዉ እስከ ጎርጎሮሳዊዉ ታሕሳስ 12015 ድረስ አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ጋዜጠኞች ሙያዊ ሐላፊነታቸዉን ለመወጣት በመሞከራቸዉ ብቻ በየሐገሩ ታስረዋል። የዋሽግተን ዲሲዉ ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሠ