1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩናይትድ ስቴት፥መካከለኛዉ ምሥራቅና አፍሪቃ

ረቡዕ፣ መስከረም 13 2002

ኦባማ እዚያዉ ኒዮርክ ከተጀመረዉ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሰሐራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎችንም አነጋግረዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/JnAm
ኦባማ፤ አባስና ናትንያሁምስል AP

በመካከለኛዉ ምሥራቅ ሠላም የማዉረዱ ጥረት ወደ ተጨባጭ ድርጊት መሸጋገር እንዳለበት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት አሳሰቡ።ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ ትናንት የእስራኤልና የፍልስጤም መሪዎችን ኒዮርክ ዉስጥ ሲያነጋግሩ እንዳሉት ሁለቱ መሪዎች በእስራኤልና በፍልስጤም መካካል ሠላም የማዉረድ ሐላፊነት አለባቸዉ።ኦባማ እዚያዉ ኒዮርክ ከተጀመረዉ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሰሐራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎችንም አነጋግረዉ ነበር።

አበበ ፈለቀ/ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ