ዩናይትድ ስቴትስ ተደጋጋሚ ፍንዳታ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 10 2005ማስታወቂያ
አሜሪካዉያን ቦስተን ዉስጥ የማራቶን ሩጫ ዉድድር እንደተጠናቀቀ በመሮጪያዉ መንገድ አጠገብ የፈነዱ ሁለት ቦምቦች የገደሏቸዉን ሰወስት ሰዎች ዛሬ-ለመዘከር ሲዘጋጁ ዌስት-ቴክስሳ ዉስጥ አንድ የማዳበሪያ ፋብሪካ ፈንድቶ ሃያ ሐይል ሰዎች ገድሏል።በመቶ የሚቆጠሩ አቁስሏል።አደጋዉ የደረሰበት ምክንያት በዉል አልታወቀም።በመሐሉ ለሐገሪቱ ፕሬዝዳት፥ ለአንድ የምክር ቤት እንደራሴና ለአንዲት ዳኛ ገዳይ መርዝ የታሸገበት ደብዳቤ ተልኮ በፀጥታ አስከባሪዎች ተይዟል።የቦስተኑን ቦምቦች አፍንድተዋል ተብለዉ የተጠጠረጠሩ ሰዎች መገኘታቸዉ ሲነገር፥ የሰዎቹ ማንነትና አላማ እስካሁን በይፋ አልተነገረም። ተደጋጋሚዉ አደጋና የአደጋ ሙከራዉን በተመለከተ የዋሽግተን ዲሲ ወኪላችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ