1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ዩኔስኮ» ፍቼ ጨምባላላን መዘገበ

ሐሙስ፣ ኅዳር 23 2008

የተባበሩት መንግሥታት የሳይንስ እና ባህል ድርጅት «ዩኔስኮ» የሲዳማ ኅብረተሰብ ባህላዊ በዓል የሆነዉን ፍቼ ጨምበላላን የሰዉ ልጅ የማይዳሰሱ ባህላዊ ሀብቶች ሥር መዘገበ።

https://p.dw.com/p/1HGnr
UNESCO United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization Logo

[No title]

ድርጅቱ ዊንድ ሆክ ናሚቢያ ላይ ባካሄደዉ አስረኛዉ ጉባኤ የኢትዮጵያዉን ይህን ባህላዊ እሴት ጨምሮ፤ የሌሎች የ11 ሃገራትን በጥቅሉ 15 ባህላዊ እሴቶችን በማይዳሰሱ ባህላዊ ሀብቶች ዝርዝር ዉስጥ ማስገባቱን ታዉቋል። ፍቼ ጫምባላላ ለሁለት ሳምንታት በተከታታይ የሚከበር የሲዳማ ህብረተሰብ የአዲስ ዓመት በላይ ሲሆን በዓሉ በሚከበርበት ወቅት የጎሳዉ የሀገር ሽማግሌዎች እና መሪዎች ለማህበረሰቡ እና ለተተኪዉ ትዉልድ ስለ ሥራ ክቡርነት ፣ መልካም አስተዳደርን እና ተግባብቶ፤ ተከባብሮ አብሮ መኖርን የሚያስተምሩበት መድረክ መሆኑን የ«ዩኔስኮ» ጋዜጣዊ መግለጫ ዘርዝሯል። ሸዋዬ ለገሠ በድርጅቱ የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ የሆኑትን ፕሮፌሰር ምትኩ ኃይለን በአጭሩ አነጋግራለች።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ