1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩኤስ አሜሪካ ሀቫና ኩባ ኤምባሲ ከፈተች

ዓርብ፣ ነሐሴ 8 2007

የዩኤስ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ዛሬ ለታሪካዊ ጉብኝት ኪውባ መዲና ሀቫና ገብተዋል። ኬሪ ከ 54 ዓመታት በኋላ በሀቫና ባለው ሜልኮ የባህር ወሽመጥ ዳርቻ የሚገኘዉ የዩኤስ አሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ዳግም በሚከፈትበት እና የሃገራቸው ሰንደቃላማ ከፍ ብሎ በሚዉለበለብበት ሥነ-ስርዓት ላይ ለመገኘት ነው ወደዚያ የተጓዙት።

https://p.dw.com/p/1GFpN
Kuba Havana Wiedereröffnung US-Botschaft Kerry
ምስል Getty Images/AFP/A. Roque

ጆን ኬሪ ከጎርጎረሳዊዉ 1945 ዓ,ም ወዲህ የኮሚኒስት መርህን የምትከተለዉን ኪውባን የጎበኙ የመጀመርያዉ የዩኤስ አሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሆናቸዉ ነዉ። ኬሪ በሃቫና ቆይታቸው ከኪውባ አቻቸዉ ቡርኖ ሮድሪገዝ ጋር በሚያደርጉት ውይይት፤ ስለ ኪውባ የሰብዓዊ መብት ይዞት እና ዩኤስ አሜሪካ በካሪቢኳ ሃገር ላይ የጣለችዉ ማዕቀብ ስለሚነሳበት፣ እንዲሁም፣ ከኪዩባ ጋር ስለተቋረጠዉ የንግድ ግንኙነት ጉዳይ እንደሚያነሱ ተገልጾዋል። በሌላ በኩል ኬሪ በኪውባ ከሚገኙ ተቃዋሚዎች ጋር እንደሚገናኙም ይጠበቃል።

Infografik Chronologie der Beziehung zwischen den USA und Kuba Englisch

ኪውባና ዩኤስ አሜሪካ ግንኙነታቸውን ከአምስት አሰርተ ዓመታት በላይ ካቋረጡ በኋላ ሐምሌ 13፣ 2007 ነበር ዳግም ዲፕሎማስያዊ ግንኙነትን የጀመሩት። ይህ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የኪውባው ፕሬዚዳንት ራዉል ካስትሮ ባለፈዉ ታሕሳስ ወር መቀራረብ ከጀመሩ በኋላ የተወሰደ ትልቁ ርምጃ መሆኑን ተያይዞ የደረሰን ዜና አመልክቶዋል።

የዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና የኩባዉ ፕሬዚዳንት ራዉል ካስትሮ የሁለትዮሽ ዉይይት የሃገራቱን ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገሩ መገለጩ ይታወሳል። የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ፓናማ ላይ በሚካሄደዉ የአሜሪካ ጉባኤ ላይ ፊት ለፊት ተገኛኝተው መነጋገራቸው ታሪካዊ ክስተት ነዉ ሲሉ የአሜሪካኑ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ተናግረዉ ነበር።

እንድያም ሆኖ ኦባማ ሁለቱ ሃገሮች እጅግ የሰፋ ልዩነት እንዳላቸዉ ሳይናገሩ አላለፉም። የኩባዉ ፕሬዚዳንት ራዉል ካስትሮ በበኩላቸዉ ሃገራቸዉ ስለሁሉም ነገ ለመወያየት ዝግጁ መሆንዋን ነገር ግን እጅግ ትዕግስት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዉ ነበር። ከጎርጎረሳዊዉ 1959 የኩባዉ ሶሻሊስት አብዮት በኋላ የዋሽንግተኑና የሃቫናዉ መንግሥት በጠላትነት ሲተያዩ መቆየታቸዉ ይታወቃል። ከባለፈዉ የጎርጎረሳዊ ዓመት 2014 ዓ,ም ጀምሮ ሁለቱ ሃገራት ለአንድ ዓመት ተኩል ከዘለቀ ምስጢራዊ ድርድር በኋላ አዲስ ግንኙነት መጀመራቸዉን ይፋ ማድረጋቸዉ ይታወሳል።

USA Kuba Beziehungen Symbolbild Fahne Flagge
ምስል Reuters/A. Harnik

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ