1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩኤስ እና ፀረ ሽብርተኝነት ትግሏ

ማክሰኞ፣ መስከረም 28 2006

ዩኤስ አሜሪካ በሶማልያ እና በሊቢያ በልዩ ኮማንዶዎችዋ ባለፈው የሣምንት መጨረሻ የወሰደችው የጥቃት ርምጃ ከአብራሪ የለሽ የጦር አይሮፕላኖችዋ ይልቅ በልዩ ኃይል ላይ ያተኮረ ሥልት መከተሏን አመላካች ሆኖ ታይቶዋል።

https://p.dw.com/p/19w7c
ምስል picture-alliance/dpa

የውጭ ግንኙነቶች ጥናት ምሁር የሆኑት ዶክተር አክባር አሊ ዩኤስ አሜሪካ በሽብርተኝነት አንፃር የተያያዘችው ዘመቻ የሥልት እንጂ የፖሊሲ ለውጥ እንደሌለው ጠቁመዋል። በሊቢያው ጥቃቱ እአአ በ1998 ዓም በታንዛኒያ እና በኬንያ የዩኤስ አሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ የተጣለው የአሸባሪዎች ጥቃት እጁ አለበት ያለችው የአል ቃይዳ መሪ ናዚህ አብዱል ሀመድ አል ራጊ በቁጥጥር ሲውል፣ በሶማልያ የባራዌ ከተማ የአሸባብ መሪዎችን ለመያዝ ያደረገችው ጥረት ከሽፎዋል።

አበበ ፈለቀ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ