1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያልሰመረው የሆረዬ ፕሮጀክት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 4 2003

ትግራይ ውስጥ በራያ አካባቢ ከዚህ ቀደም የተጀመረው ሆረዬ የተባለው ፕሮጀክት ውጤት አለማምጣቱን ገበሬዎች አስታወቁ ።

https://p.dw.com/p/RfB6
ለውሐ ማቆሪያ የታሰቡት ላስቲኮች በጣሪያ ላይምስል DW

ገበሬዎቹ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ከላይ የወረደ መመሪያ ነው ተብሎ የተጫነባቸው የውሐ ማቆር ሥራ ጉልበት ከማባከን በስተቀር አንድም ጥቅም እንዳላስገኘላቸው ተናግረዋል ። ይልቁንም ለዚሁ ሥራ ተብሎ የታደለውን ላስቲክ ለታሰበለት የውሐ ማቆሪያ ሳይሆን ለቤት ክዳንና ሌሎች ግልጋሎቶች ጥቅም ላይ ማዋላቸውንም አስታውቀዋል ። ሥራው ውጤታማ ያልሆነበት ምክንያት በቂ ጥናት ተደርጎ ባለመጀመሩ መሆኑን በወቅቱ በዚህ ስራ ላይ የተካፈለ አንድ የእርሻ ልማት ሰራተኛ ተናግሯል ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከመቀሌ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ