1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ያልታየዉ ተዉኔት» ከደምሰዉ መርሻ

ሰኞ፣ ጥቅምት 22 2008

«ወቅቱ ክረምት ነዉ ካፊያ የሚጥልበት፤ መንገዱ ጠባብ ነዉ፤ ኮሮኮንች የበዛዉ ሰዉ የማይሄድበት፤ ላይጨልም ጨልሞ አይን ያጭበረብራል፤ ይህ የሕይወት አረም ወቅትን ተገን አድርጎ፤ ዓይንን ከጋረደ ማ ማንን ይለያ።»

https://p.dw.com/p/1GyFf
Äthiopien Demisew Mersha CD Cover Titel Yaltayew Tewnet
ምስል Demisew Mersha

«ያልታየዉ ተዉኔት» ከደምሰዉ መርሻ


ገጣሚ ደምሰዉ መርሻ ከጥቂት ወራቶች በፊት «ያልታየዉ ተዉኔት» በሚል ርዕስ በሲዲ ካሳተመዉ የግጥም ሲዲዉ የተወሰደ ስንኝ ነዉ ። ገጣሚ ደምሰዉ መርሻ ግጥሞቹን ለምን በመጽሐፍ አላሳተመም?

«ሲዲ»ን የመረጥኩበት ልዩ ምክንያት፣ ይላል ገጣሚ ደምሰዉ፣
« የግጥም መጽሐፎች የሚታተሙት በቁጥር ከሶስት ሺህ እስከ አምስት ሺህ በመሆኑ እና ወጭዉ የጎላ በመሆኑ ነዉ። በሲዲ ከሆነ ማኅበረሰቡ ጋር ቶሎ የመድረስ አቅሙ የጎላ ነዉ። ሀሳብን ቶሎ ለማስተላለፍ እና ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ፤ ከማንበብ ወደ ማድመጡ እናደላለን በሚል፤ የተሻለ ይሆናል የሚል ሃሳብን ይዤ ነዉ።»

ግን በ«ሲዲ» ግጥሞችን የማዳመጥ እድል የሌላቸዉ የኅብረተሰቡ ክፍሎች የአንተን ግጥሞች እንዴት ሊያገኙ ይችላሉ? ለዚህና ለሌሎች የተለያዩ ጥያቄዎች ገጣሚ ደምሰዉ መርሻ መልስ አለዉ። ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።

አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሃመድ