1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳናዉያን ስደተኞች በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 20 2008

በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን «UNHCR» ቢሮ እንደገለፀዉ፤ በአፍሪቃዉ ቀንድ ከሚገኙ ሃገሮች ኢትዮጵያ ከ 735 ሺህ በላይ ስደተኞችን በመቀበል የመጀመርያዋ ሃገር ስትሆን ከነዚህ መካከል 270 ሺዉ ደቡብ ሱዳናዉያን መሆናቸዉንና ዘጠና በመቶዉ ደግሞ ሴቶችና ሕጻናት እንደሆኑ ገልፆአል።

https://p.dw.com/p/1IenY
Symbolbild Frauen Opfer Konflikt Südsudan
ምስል GetttyImages/AFP/C. Lomodon


በደቡብ ሱዳን ለሁለት ዓመታት በዘለቀዉ ጦርነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸዉን ጥለዉ ተሰደዋል። ላለፉት ሁለት ዓመታት የደቡብ ሱዳን አማፂ ቡድንን የመሩት ሪክ ማቸር ከትናንት በስትያ ጁባ ተመልሰዉ የብሔራዊ የአንድነት መንግሥት ምክትል ፕሬዝደንት ሆነዉ ቃለ ከፈፀሙ በኋላ በሃገሪቱ ሠላም ሰፍኖ በጋምቤላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሃገራቸዉ ሊመለሱ ይችላሉ የሚል ተስፋ ይኖር ይሆን? በመጠለያ ጣብያዉ የሚገኙት ደቡብ ሱዳናዉያን ስደተኞችስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? አዜብ ታደሰ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን «UNHCR» የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔርን አነጋግራለች።


አዜብ ታደሰ


ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ