1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳንና የሰላሙ ጥረት

ሰኞ፣ ጥር 25 2007

የተፈረመው ሰነድ፤ የሥልጣን ክፍፍልን የሚመለከት አለመሆኑን፤ የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት አዳራዳሪ አካል አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/1EUf2
ምስል Reuters/T. Negeri

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች፤ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረውን ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ውጊያ እስካሁን መግታት አልቻሉም። በመሆኑም ፤ ተኩስ አቁመው ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት ከመመሥረታቸው በፊት፤ ያንኑ ቅድመ ዝግጅት በሚያመቻችላቸው ሰነድ ላይ መፈረማቸው ተንግሯል። የተፈረመው ሰነድ፤ የሥልጣን ክፍፍልን የሚመለከት አለመሆኑን፤ የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት አዳራዳሪ አካል አስታውቋል። ሁለቱ ወገኖች ከ4 ቀናት ድርድር በኋላ ሥልጣን ለመጋራትና የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምተዋል ሲሉ በርካታ የሃገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ,ቀትር በፊት ዘግበው ነበር ። ኪር በፕሬዝዳንትነታቸው እንደሚቀጥሉ ተቀናቃኛቸው ማቻር ደግሞ የቀድሞውን የምክትል ፕሬዝዳንትነት ሥልጣናቸውን እንደገና እንደሚረከቡ ነበር የተዘገበው ።በስምምነቱ መሠረት ገዥው ፓርቲ የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ በምህፃሩ ኤስ ፒ ኤል ኤም ከምክር ቤቱ መቀመጫዎች 53 በመቶውን እንደሚይዝ ማቻርን የሚደግፈውን ቡድን ጨምሮ የተቀሩት ሁለት የንንቅናቄው አንጃዎች ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር 33 መቀመጫዎች እንደሚወስዱም በስምምነቱ መጠቀሱ ነበር የተገለፀው ።ሆኖም ዳክ በአሁኑ ሰነድ ላይ የወደፊቱን አስተዳደር አወቃቀርም ሆነ ሥልጣን መጋራትን የተመለከተ አንዳችም ስምምነት የለም ሲሉ ማስተባበላቸውን ሱዳን ትሪብዩን ዘግቧል ። ዳክ የመጨረሻ የሰላም ስምምነት ላይ ከተደረሰ ሐምሌ 2 ፣ 2007 ዓም የሽግግር መንግሥት እንደሚመሠረት መናገራቸውን ሱዳን ትሪብዩን የተባለውን ጋዜጣን ጠቅሶ የጀርመን ዜና አገልግሎት ዲ ፒ ኤ ዘግቧል ።ኪርና ማቻር በመጪው የካቲት 13 ፣ 2007 በሌሎች ቀሪ ጉዳዮች ላይ ተጨማሪ ድርድሮችን ለማካሄድም ቃል መግባታቸው ተዘግቧል ።

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ