1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ ሱዳን የፆታ ጥቃት

ሐሙስ፣ ግንቦት 11 2008

በጥናቱ መሠረት ደቡብ ሱዳን ነፃነቷን ካወጀች ወዲሕ በተቆጠሩት አምስት ዓመታት ዉስጥ ከ10 ሺሕ በላይ ሴቶችና ልጃገረዶች ተደፍረዋል

https://p.dw.com/p/1Iqli
ምስል Tierärzte ohne Grenzen

[No title]

የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሐይላት ከጠላታቸዉ የወገነ ማሕበረሰብን ለማጥቃት የማሕበረሰቡን ሴቶችና ልጃገረዶችን መድፈር፤ ማገትና ማንገላታትን እንደ ወታደራዊ ሥልት መጠቀማቸዉን የመብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታወቁ።አምንስቲ ኢንተርናሽናል ያስተባበራቸዉ ድርጅቶች ያደረጉት ጥናት እንዳመለከተዉ ደቡብ ሱዳን ዉስጥ ሴቶችና ልጃገረዶችን መድፈርና ማገት በጦርነቱ ወቅት አልቅጥ ቢባባስም ከጦርነቱ በፊትም በተደጋጋሚ ይፈፀም ነበር።በጥናቱ መሠረት ደቡብ ሱዳን ነፃነቷን ካወጀች ወዲሕ በተቆጠሩት አምስት ዓመታት ዉስጥ ከ10 ሺሕ በላይ ሴቶችና ልጃገረዶች ተደፍረዋል።ሥለ ጥናቱ ዉጤት የናይሮቢ ወኪላችንን በሥልክ አነጋግረነዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ