1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድላሚኒ ዙማ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽነር

ሰኞ፣ ጥቅምት 5 2005

ለአፍሪቃ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሆነው ከሁለት ወር ተኩል በፊት የተመረጡት የቀድሞዋ የደቡብ አፍሪቃ ባለስልጣን- እንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ- ዛሬ መንበራቸውን በይፋ ተረክበዋል።

https://p.dw.com/p/16QVj
ንኮሳንዛና ድላሚኒ ዙማምስል Reuters

ከቀድሞው አቻቸው ተሰናባቹ ዣን ፒንግ ስልጣኑን የተረከቡት ድላሚኒ ዙማ በአፍሪቃ ኅብረት ትልቅ ኃላፊነት እንደሚጠብቃቸዉ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።

ከእሳቸዉ አስቀድሞ በኃላፊነት ላይ የነበሩትን ለጥረታቸዉ በማመስገንም በማሊ፤ ሱዳንና ሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋ በመተባበር ለማስወገድ እንደሚሠሩ አመልክተዋል፤
«ስለዚህ ጥረታችንን አሰባስበን በማሊና ሳህል አካባቢ ያሉ ግጭቶችን ለማስወገድ እንጥራለን። እስካሁን ችግሩን ለማስወገድ እየሞከሩ ካሉት ከተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት እና ከአካባቢዉ ድርጅት ECOWAS ጋ በቅርበት ለመስራት እንሞክራለን። ሱዳንና ደቡብ ሱዳንን እንዲረዳም ለአፍሪቃ ከፍተኛ የሽምግልና መድረክም አስፈላጊዉን ድጋፍ መስጠታችንን እንቀጥላለን።»
በአፍሪቃ ኅብረት ታሪክ ሴት ከፍተኛ የመሪነት ስልጣን ስትይዝ ንኮሳዛና ድላሚኒ ዙማ የመጀመሪያዋ ናቸዉ። ዙማ ሀገራቸዉ ደቡብ አፍሪቃን በዉጭ ጉዳይና በአገር ዉስጥ ጉዳይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል።

Gipfel Afrikanische Union Addis Abeba
ምስል dapd

የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ በአፍሪቃ ህብረት የተካሄደውን የስልጣን ርክክብ ስነ-ስርዓት ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ