1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድርቅ፣ ረሀብ እና የርዳታ ማፈላለጊው ስብሰባ በሮም

ሰኞ፣ ሐምሌ 18 2003

በአፍሪቃ ቀንድ ሀገሮች ለሚገኙት ወደ አስራ ሶስት ሚልዮን ለሚጠጉት የድርቅ ሰለባዎች አስቸኳይ እና ግዙፍ ርዳታ እንደሚያስፈልግ ዛሬ የተመድ የምግብና የርሻ ድርጅት ፋኦ ኃላፊ ዣክ ዲዮፍ ዛሬ ረፋዱ ላይ በሮማ ኢጣልያ በተከፈተው ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ አሳሰቡ።

https://p.dw.com/p/Rc0z
ምስል AP

አሁኑኑ አጣዳፊ ርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር በነዚህ ሀገሮች ፡ በተለይ ድርቁ አብዝቶ በጎዳት በሶማልያ ሁኔታዎች እየከፉ እንደሚሄዱ ዲዩፍ አስጠንቅቀዋል። ለጋሽ ሀገሮች ርዳታ ለማቅረብ ቃል ቢገቡም፡ እስካሁን ለተጎጂዎች የደረሰው ገንዘብ በጣም ንዑስ መሆኑ ነው የተገለጸው። ፋኦ ያስተናገደው ይኸው በሮማ በመካሄድ ላይ የሚገኘውን የዛሬውን ስብሰባ የሮማው ወኪላችን ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ ተከታትሎታል። ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት አነጋግሬዋለሁ።

አርያም ተክሌ

ሒሩት መለሰ