1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድርቅ በደቡብ ኦሞ ዞን

ሐሙስ፣ ኅዳር 29 2009

በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የተከሰወዉ የዝናብ እጥረት እና ድርቅ ከብቶችን እየገደለና እየጎዳ መሆኑን የአካባቢዉ ኗሪዎች አመለከቱ። አንድ የአካባቢዉ ነዋሪ በተለይም በና ፀማይ ወረዳ በርከት ባሉ ቀበሌዎች ሕዝቡ ከዚህ ቀደም ከሚከሰተዉ የከፋ መሆኑን የሚናገርለት ይህ ድርቅ ብዙ ከብቶችን እየገደለ መኖሆኑን ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

https://p.dw.com/p/2TuDz
Äthiopien Dürre in Gelcha
ምስል Reuters/T. Negeri

Drought in South Omo zone - MP3-Stereo

 በሚመለከተዉ የመንግሥት አካል ድርቁ ስላደረሰዉ ጉዳት ቅኝት እና ጥናት እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት እኚሁ ነዋሪ እንደሚሉትም በአካባቢዉ ነዋሪዎች ግምት ከመስከረም ወር አንስቶ ብቻ ከ6 ሺህ የሚበልጡ ከብቶች አልቀዋል። አካባቢዉ የአርብቶ አደሮች መኖሪያ እንደመሆኑም ችግሩ የከፋዉ በከብቶቹ ላይ መሆኑንም ገልፀዉልናል። 2

ድርቁ በአካባቢዉ ባጠቃላይ የሚታይ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪ በተለይ ግን በፀማይ 10 እና 11 የሚሆኑ ቀበሌዎች ላይ እንደጠና፣ ከፊል ሐመርም በዚሁ ችግር ተጎጂ መሆኑንም ዘርዝረዋል። ሕዝቡ ከዚህ በፊት አይተንና ሰምተን የማናዉቀዉ ባለዉ ድርቅ ምክንያትም ከሌላ አካባቢዎች የከብቶች መኖ ተጭኖ እስኪመጣ የደረሰ ቢሆንም የክልሉን ገፅታ ለመጠበቅ በሚል የደረሰዉ እና የሚደርሰዉ ጉዳት ብዙም አልተነገረለትምም ይላሉ። የክልሉን የግብርና እንዲሁም የአደጋ መከላከል እና ፀጥታ ምላሽ ቢሮዎች ለማግኘት በተደጋጋሚ ያደረግነዉ የስልክ ጥሪ አልተሳካም። የብሑራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሣ የተከሰተዉ ድርቅ እንደሚታወቅ እና የሕዝቡ የኑሮ ዋልታ የሆኑትን የከብቶቹን ሕይወት ለማትረፍም ጥረቶች እየተደረገ ነዉ ይላሉ።

አክለዉም አቶ ምትኩ በደቡብ እና ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚጠበቀዉ ዝናብ በወቅቱ አለመዝነቡንም ራሳቸዉ መናገራቸዉን በማስታወስ በድርቅ ለተጎዱት አካባቢዎች በመፍትሄነት እየተሠሩ ስላሉት ሥራዎችም እንዲህ ገልፀዋል። አካባቢዉ የአርብቶ አደሮች መኖሪያ እንደመሆኑ ድርቁ ቀጥታ ተፅኦኖዉን ያሳረፈዉ በከብቶቻቸዉ ላይ ነዉ። ኅብረተሰቡንስ አያሰጋዉ ይሆን?

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ