1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ድርቅ እና የ«ኦቻ» መግለጫ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 16 2009

በኢትዮጵያ በድርቅ የተጎዱት ዜጎች ቁጥር ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአምስት ሚልዮን ስድስት መቶ ሺህ  ወደ ስምንት ሚልዮን አምስት መቶ ሺህ አሻቅቧል። ከዚህ በተጨማሪም፣ በተለይ በሶማሌ ክልል አርብቶ አደሮች በድርቁ ሰበብ የገቢ ምንጫቸው የሆኑ ብዙ እንሰሳትን ማጣታቸውንም የተመ የምግብ እና የእርሻ ድርጅት፣ በምህጻሩ «ፋኦ» ባለፈው ሳምንት ገልጿል።

https://p.dw.com/p/2ieEp
Äthiopien Gode - Dürre-Krise
ምስል DW/J. Jeffrey

የድርቁ መዘዝ በተለይ በአርብቶ አደሮች ኑሮ ላይ ጫና አሳርፏል።

ለነዚሁ ተጎጂዎች መርጃ አንድ ቢልዮን ዶላር እንዲቀርብ ቀደም ሲል በተመድ ተጠይቆ የነበረው ርዳታ አሁን ወደ አንድ ቢልዮን አምስት መቶ ሚሊዮን ዶላር ከፍ ሊል እንደሚገባ ተገልጿል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ