1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶቸ ቨለ በሥራ አስኪያጁ ዓይን

ሰኞ፣ ሚያዝያ 28 2005

የጣቢያው ዋና ሥራ - አስከያጅ ሁኜ ኃላፊነቱን ከመረከቤ በፊት ይህ ሁኔታ ግልጽ ያደረገልኝ ነገር ቢኖር፣ እንደ ዶቸ ቬለ ያለ ትልቅ ተቋም ለአንድ አገር ፣ እንደ ጀርመን ያለ አገር፣ በእራሱ ቋንቋ፣ የእራሱን አቋም ለውጩ ዓለም ለማሰማት የሚችልበት መገልገያ መሣሪያ መጨበጡ፣ ምን ያህል

https://p.dw.com/p/18R3j
Erik Bettermann, Intendant der Deutschn Welle
ዋና ሥራ አሥኪያጅ ኤሪክ በተርማንምስል DW

ዶቸ ቨለ ሥርጭት የጀመረበትን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከጣቢያዉ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ከኤሪክ በተርማን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ጥያቄ  ዶቸቬለ:-

በአለፉትአሥራሁለትዓመታት፣በእነዚህየሥራዘመናት፣ማለትከዘመኑመለወጫከሚሌኒዩምጊዜጀምሮእስከአሁንድረስ፣በጣቢያው:በዶቸቬለላይአሻራውንጥሎ፣ወሰኝሁኖየሄደነገርምንድነው? ምንይመስሎታል? (ትንሽማብራሪያይሰጡናል? )

መልስ፤  ኤሪክቤተርማን:-

የፖለቲካውንዓለምከወሰድነውናከተመለከትነውአለጥርጥርበመስከረም11 በ2001 (እ.ጎ.አ.) ኒውዮርክከተማላይየወረደውመዓትናእሱንተከትለውየተከሰቱትሁኔታዎችናቸው።የጣቢያውዋናሥራአስከያጅሁኜኃላፊነቱንከመረከቤበፊትይህሁኔታግልጽያደረገልኝነገርቢኖር፣አንድጉዳይነው።እሱም፣  እንደዶቸቨለያለትልቅተቋምለአንድአገር፣እንደጀርመንያለአገር፣በተለያየቋንቋ፣የእራሱንአቋምለውጪዉዓለምለማሰማትየሚችልበትመገልገያመሣሪያመጨበጡ፣ምንያህልትልቅነገርእንደሆነለመረዳትአስችሎኛል።ከዚህባሻግርሌላምጉዳይአለ።በትልቅፍጥነትናወደፊትበዓይናችንሥርየሚራመደውየቴክኒክዕድገትነው።ይህምበግልጽበዓለምአቀፍደረጃየመገናኛብዙሃኑንአገልግሎትናአውታሮቹን፣እንዳለ፣አብዮትልንልእንችላለን፣ቀያይሮታል።ይህምአዲስሁኔታ፣  የጋዜጠኞችንየአእምሮሥራናሥርጭቱንጭምር፣ከዚያምአልፎየተገልጋዩናየተጠቃሚውንምሕዝብ፣ባሕሪእንዳለቀይሮታል።

ጥያቄ  ዶቸቨለ:-

የሁለተኛዓለምጦርነትከቆመከስምንትዓመትበኋላሥርጭቱንየጀመረውዶቸቨለሁለትዓላማነበረው።አንደኛውበጀርመንላይተለጥፎየነበረውንመጥፎአመለካከትአለዝቦየአገሪቱንአዲስጎዳናለዓለምሕዝብማሳየትነበር።ሌላው፣ወደዓለምአቀፉማህበረሰብየተመለሰቺውንጀርመንንበጣቢያውሥራአብሮማጀብምነበር።

ጥያቄ ዶቸ ቨለ፦

አሁንከዚያከስድሳአመት፣የሥራዘመንበሁዋላ፣የጣቢያውየወደፊትግደጅናተግባርምንድነውብለውያስባሉ፣ይገምታሉ?

Interview mit Bundeskanzler: Konrad Adenauer und DW-Redakteur Hans Wendt im Jahr 1963 Copyright: H. Bogler Datum unbekannt Bild geliefert von DW/Alexandra Schottka für DW/Monika Griebeler.
የቀድሞዉ የጀርመን መራሔ መንግሥት ኮንራድ አደናወር ከዶቸ ቬለ ጋዜጠኛ ጋር በ1963 (አጎአ)ምስል DW

መልስ  ኤሪክቤተርማን:-

ያኔምሆነአሁንየዶቸቨለዋናየሥራአቅጣጫ፣አገራችን፣የምትመራበትናአገራችንትክክልነውብላየተቀበለቻቸውንእሴቶችበሙሉ፣ሌሎቹእንዲረዱትወደወጪማስፋፋትነው።ዶቸቨለበ2005 እ.ጎ.አ. ያወጣውደንቡንለመጥቀስ«ጀርመን  በአበበውናበደራውየአውሮፓትልቅሥልጣኔውስጥ፣በሕግየበላይነትየሚመራና የሚታመን፣ነጻናዲሞክራቲክሥርዓትንየተቀበለችመንግሥትመሆኑዋን፣ማሳየትአንደኛውተግባሩነው።» የሚልአረፍተነገርይገኝበታል።ይህመመሪያበብዙመንገድየአሰራራችንንመስክሰፋአድርጎአሻሽሎአሰቀምጦልናል።እንግዲህበተለያዩቋንቋዎችየምናሰራጫቸውሐሳቦችናአስተያየቶች፣ከዚሁምጋርበአካዳሚውበኩልለወጣትጋዜጠኞችየምንሰጠውትምህርትን፣አጠቃለንስንመለከት፣የተለያዩባህሎችናሥልጣኔዎች፣ከእኛምከጀርመኑምጋር፣ሐሳብበቀናመንገድየምንለዋወጥባቸውናየምናሸራሽርባቸው፣መድረክምነው። 

እንግዲህእኛእራሳችንንየምናየው፣እንደነጻነትድምጽናልሣን፣እንደሰበአዊመብትተሟጋችነው።ሌላምኃላፊነትአለብን።የጀርመንቋንቋምእናስተምራለን።

 ጥያቄ  ዶቸቨለ:-

ይህንእንዴትነው፣በተጨባጭበተለያዩቋንቋዎችእናበተለያዩአካባቢዎች፣በሥራየምትተረጉሙት?

 መልስ  ኤሪክቤተርማን:-

ዋናውአላማችንበዓለምዙሪያየሚገኙትንብዙውንአካባቢማዳረስነው።ለዚህምነውበተለያዩሰላሳቋንቋዎችፕሮግራማችንተዘጋጅቶየሚሰራጨው።

ጣቢያውበምን፣በምንላይማተኮርእንዳለበትበውስጥደንቡናበተነደፈውመመሪያአላማውስለሰፈረ፣የዝግጅትክፍሎቹ፣ይህንመስመርተከትለውሥራቸውንይሰራሉ።ግንደግሞየቴለቪዠንተመልካቾቻችን፣የራዲዮአድማጮቻችን፣የኢንተርኔትተጠቃሚዎቻችንምከእኛበየጊዜውለመስማት፣ለማዳመጥወይምደግሞለማየትየሚፈልጉትንነገር(ማሳወቃቸዉ)ሥራችንንለመተለምለእኛወሳኝነው።

እንግዲህእንደአካባቢውናእነደሁኔታውበተለያዩቦታዎች፣በተለያዩቋንቋዎች፣በተለያዩአቀራረቦች፣የእነሱንፍላጎትለማሟላትጥረትእናደርጋለን።

በየጊዜውበአፋጣኝሁኔታከሚቀያየረውየቴክኒክዕድገትምጋር፣አብሮየሚለዋወጠውናየሚቀያየረውንየተጠቃሚዎቹን፣ባህሪናመንፈስ፣  እኛተገንዝበንከእነሱጋር፣አብረንመራመድ  አቀራረባችንምመቀየር  ይኖርብናል።

የአጭርሞገድየራዲዮስርጭትለረጅምአመታትየተጠቀምነውበዚሁምክንይትነው።በሁዋላምየሳተላይትቴሌቪዠንምያስፋፋነው፣ቆይተንምበኢንተርኔትላይያተኮርነው፣አሁንደግሞበሁለ-ገቡ(መልቲሚዲያ)ላይቆርጠንየገባነው።

እንግዲህግልጽለማድረግ፣ለተለያዩአካባቢዎችየተለያዩአቀራረቦችአሉን።ከአንድአመትጀምሮለስድስትአካባቢዎችበጀርመንኛናበእንግለዘኛ፣በስጳኝናበአረብኛቋንቋ፣በቴሌቪዠንፕሮግራማችንየተለያዩዝግጅቶችናዜናዎችንለእነሱእናስተላልፋልን።

በተቀሩትየተለያዩቋንቋዎችደግሞለወዳጅየቴሌቪዠንጣቢያዎች(የቴሌቪዠን)ፕሮግራሞችአዘጋጅተንበዓለምዙሪያ፣እናሰራጫለን።በኦንላይንእንቅስቃሴምላይተሳትፈንየተጠቃሚዎቻችንንፍላጎትእናሟላለን።

ጥያቄ  ዶቸቨለ

(hinten v. l.) Jean-Yves Bonsergent (AEF), John Maquire (AEF), Tetsushi Wakita (NHK), David Ensor (VOA) - (Mitte v. l.) Mark Bunting (BBC), Peter Horrocks (BBC), Richard Lobo (BBG), Lynley Marshall (ABC), Robert Zaal (RNC), Jim Egan (BBC) - (vorne v. l.) Erik Bettermann (DW), Klaus Bergmann (DW), Bernadatte van Dijcke (RNW)
በተርማንምስል DW

ሕግአውጪውየሰጠውየመተዳደሪያደንብያለውድርጅት፣በመንግሥትድጎማየሚንቀሳቀስጣቢያ፣(እስቲበትንሹምቢሆንያብራሩልን፣) እንዴትአድርጎነውከመንግሥት፣ከፖለቲካጣልቃገብነት፣ገለልተኛየሆው?የጋዜጣኝነትመብትንአስጠብቆ፣ያለፉትንስድሳአመትያሳለፈው? በዚህአጣብቂኝበሆነሁኔታውስጥተቀምጦጣቢያው፣እንዴትአድርጎነው፣ገለልተኛእናየሚታመንተደማጭነትያለው፣ጣቢያሁኖሊወጣየቻለው?

  መልስ  ኤሪክቤተርማን:-

በእርግጥየስርጭቱኢላማበውጪአገሮችላይየሆነውጣቢያ፣ሥራውንየሚያካሄድበትበጀቱን  የሚያገኘውመንግሥትበቀረጥናግብር፣ከሕዝብከሚሰበስበውገንዘብነው።በአንድበኩልበዚህሁኔታበዓለምአቀፉየዜናሥርጭትላይከሌሎቹጋርእኩልእንሳተፋልን።በሌላበኩልእንደማንኛውምየሕዝብመገናኛዘዴእኛምበሕገ-መንግሥቱ፤ አንቀጽአምስትላይየሰፈረውን፣የፕሬስነጻነትእንጠቀማልን።

ከሕዝብበቀረጥመልክከተሰበሰበውየመንግሥትገንዘብከሚገኘውድጎማሥራችንንበማካሄድናገለልተኛነጻጋዜጠኛሁኖእለታዊሥራንበማከናወን መካከልምንምዓይነትቅራኔየለም።ዶቸቨለ በአልተዛባ፣ሚዛኑንበጠበቀአሰራሩናበጥሩጋዜጣዊአቀራረቡ፣በአለፉትየረጅምአመታት፣ምንነቱን፣አስመስክሮ፣ጣቢያዉ በብዙዎቹዘንድተቀባይነትንአግኝቷል።

ይህጣቢያምበገዛአገራቸው፣ተጨቁነውድምጻቸውንማሰማትየማይችሉወገኖችናግለሰቦች፣ድምጻቸውንየሚየያሰሙበት፣ልሣንነው።ብዙዎቹይተማመኑብናል።ብዙዎቹምሥራችንንትክክልነውብለውተቀብለውታል።እንደዚህዓይነቱንእምነትማግኘትደግሞበዓለምአቀፍደረጃለሚንቀሳቀስአንድየራዲዮናየቴሌቪዠንጣቢያበገንዘብየማይገዛትልቅሐብትነው።     

  ጥያቄ  ዶቸቨለ

ምናልባትበዓለምአቀፍደረጃ፣የዶቸቨለአካዳሚተወዳጅየሆነው፣በዚህምክንያት ይሆን? 

በዓለምደረጃነጻናለማንምክፍትየሆነ፣ግልጽየዜናማሰራጫ፣የተለያዩሐሳቦችማንሸራሸሪያ፤ሚድያይስፋፋ፣ይጠንከርእያልንንስንጠይቅናስንከራከር  ቢያንስሃምሳዓመትይሆነዋል።

ከጀርመንየልማትተራድዕ ሚኒስቴርጋርሆነን፣በታዳጊአገሮች፣የጋዜጠኞችንአሰራርናጥራት፣ችሎታናአቀራረብለማሻሻል እንጥራለን።እውንቱንለመናገርጥረታችንጋዜጠኞችንከማሰልጠንአልፎምየሚሄድነው።የሚዲያ አውታሮች እና ተቋሞች፣ በታዳጊ አገሮች እራሳቸውን በእራሳቸው በኢኮኖሚ ችለው ፣ሊንቀሳቀሱ የሚችሉበትን እስትራተጂ መንደፍና ማሳየቱ አንደኛው ሥራችን ነው። ምንም ዓይነት የዜና መለዋወጫና መገናኛ ዘዴ የሌላቸውን ፣ የተረሱና የተጨቆኑ፣ የተበደሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን፣ማስተናገድ ሌላው የሥራ መስክና አትኩሮታችን ነው።

360°, Virtueller Rundgang, My DW, 60 Jahre DW. Vermerk: ***Nur für My DW zu verwenden*** 360 Grad/360° Copyright: My DW
ምስል My DW

በተደጋጋሚ በተለያዩ አካባቢዎችና አገሮች፣ በመንግሥት ሙሉ ቁጥጥር ሥር የነበሩ የተለያዩ የቴሌቪዠን እና የራዲዮ ጣቢያዎች፣ ነጻ- ሆነው ፣ ነገር ግን   አመታዊ የሥራ ማካሄጃ በጀታቸውን፣ ከሕዝብ ከተሰበሰበ  ቀረጥ ፣አግኝተው ፣ እኛ እንደምደርገው፣ ገለልተኛ ዜናን ለሕዝባቸው እንዲያቀርቡ፣ ሕዝባቸውንም እንዲያገለግሉ በምክራችን ብዙዎቹን  እዚያ ደረጃ ላይ አድረሰናቸዋል።

በቅርቡ ከሰራነው መሐል የሞልዶቫው ሪፓብሊክ አንዷ ናት። እኛም ጋ ኑ እንጂ የሚሉ ጠያቂ አገሮች ቁጥር ብዙ ነው። ግን የሁሉንም ጥያቄ አቅማችን ውስን ስለሆነ እንደምንፈልገው ሟሟላት አንችልም።ያም ሆኖ በየአመቱ ፣ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ጋዜጠኞችንና የሚዲያ ሰዎችን እዚህ አምጥተን እናሰለጥናለን። በሌላ በኩል እኛም እዚያው ታዳጊ አገሮች እየሔድን በቦታው ተገኝተን ፣ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደን፣ እናሰለጥናለን።

በአካዳሚአችን በኩል በማስተርስ ዲግሪ ጥናት አንድ ወጣት የሚማመረዉ  የዓለም አቀፉ የሚዲያ ትምህርት ደረጃን የጠበቀና ከወዳጅ አገሮች ተኮትኩተው የሚወጡበት መስክ ነው። እንደሚታወቀው፣ የዶች ቬለ አካዳሚ በዓለም አቀፉ የሚዲያ ጥናትና ምርምር፣ አንደኛውና የመሪውን ቦታም የያዘ  ተቋም ነው።            

ጥያቄ  ዶቸ ቨለ፦

በአጭር ሞገድ የራዲዮ አገልግሎት፣ ለረጅም አመታት  የሚታወቀው ዶቸ ቨለ፣

ወደ ሁለ-ገብ መልቲሚዲያ ድርጅት አድጎ ሊቀየር ችሎአል። ይህ ሊሆን የቻለው በምን ምክንያት ነው? ለጊዜው አንገብጋቢ ጥያቄ ፣ ጊዜው፣ የሚጠይቀውን አስቸኳይ መልስ፣ ለመስጠት ታስቦ ነው?

መልስ  ኤሪክ ቤተርማን:-

ሥርጭታችንን ከጀመርንበት ከ1953 (እ.ጎ.አ) ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ዓለም ዓለም የራዲዮ አገልግሎት እና ፣ ዓለም አቀፉ የመገናኛ ዘዴዎች፣ በአፋጣኝ ሁኔታ እየተቀያየሩ፣ ሄደዋል።ከጊዜው ጋር አብሮ የማይሄድና የማይራመድ፣ ለጊዜውም ጥያቄ መልስ በአስቸኳይ ማቅረብ የማይችልና የሚሳነው ጣቢያም፣ አንድ ቀን ተተፍቶ፣ ከጨዋታው ውጭ እንደሚሆን፣ የታወቀ ነው። ይህን ተገንዝበን እኛም ቶሎ ብለን በዲጅታል ሥራ ላይ አተኩረን በእሱ መገልገልና ዜናዎቻችን ማሰራጨት ጀመርን። እንግዲህ እኛ ነን በጀርመን አገር፣ በህዝብ ገንዘብ ከሚተዳደሩ የራዲዮ ጣቢያዎች ሁሉ ፣ ሌሎቹን ቀድመን በኢነተርኔት፣ መጠቀም የጀመርነው።

Treffen von Vertretern führender Auslandssender Mitte Dezember 2012 in Berlin
በተርማን ከዓለም አቀፍ ማሠራጫ ጣቢያዎች ሐላፊዎች ጋርምስል DW

በዚያውም መጠን እኛ ነን ፣ ግንባር ቀደም ሆነን፣ ሁለገቡን (መልቲ)ሚዲያውን ጨብጠን ወደፊት የተራመድነው። እንግዲህ ዕወቀት ለመሰብሰብና የጋዜጠኛ የሥራ ልምድ ለማካበት፣ እኛ ጋ መጥቶ ለጥቁት ወራት ለመሰንበት የሚፈልግ አንድ ሰው ቢኖር፣ በሁሉም ሜዳ ሰልጥኖ …ካሜራውንም፣ ብዕሩንም፣ ድምጽ አቀዳዱንም፣ አቆራረጡንም ፣ በኢንተርኔት አሰራጨቱንም፣….ምንም ሳይቀር፣ ሁሉንም ተምሮና  እራሱን ችሎ፣ አገሩ ይገባል። 

እነዚህ ሁሉ፣  ሁለ-ገብ የአሰራር መስኮች ደግሞ ፣  በተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች፣ በሰላሳውም የዝግጅት ክፍላችን ውስጥ፣ ጋዜጠኞቻችን በየዕለቱ የሚያንከባልሉት፣ የሚያቀላጥፉት ፣ ሥራ ነው።

In dialogue with the world

ካትሪን ቬስክ

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ