1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶ/ር መረራ ጉዲና የፍርድ ቤት ውሎ

ሐሙስ፣ ጥር 18 2009

ከአውሮጳ ጉዞ መልስ ወደ ሁለት ወራት ገደማ የታሰሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር የዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቆች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ። ጠበቆቻቸው የክስ ሒደቱ እንዲጀመር ያቀረቡት ጥያቄም ውድቅ ሆኖ የዶ/ር መረራ ጉዲና ጉዳይ ለየካቲት 16፣ 2009 ዓም ተቀጥሯል። 

https://p.dw.com/p/2WT1P
Dr. Merera Gudina Addis Abeba Äthiopien Oromo Pressekonferenz PK
ምስል DW/Y.Egziabhare

mmt Ethiopian Court adjourned Dr Merera’s case - MP3-Stereo

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሊቀ መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቆች ዛሬ ታኅሳስ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆኗል። አንድ ተጠርጣሪ የዋስትና መብት የሚከለከለው ማስረጃዎች ያጠፋል፤ ምስክሮችን ያባብላል፤ ወንጀል ይፈፅማል አሊያም ከሐገር ይኮበልላል የሚል ሥጋት ሲኖር ብቻ ነው ይላሉ ከዶ/ር መረራ ጉዲና ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም።  ዶ/ር መረራ ከእነዚህ ስጋቶች ነፃ ናቸው በሚል እምነት ዋስትና መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ጠበቃው ከምርመራ በኋላ ክስ በይፋ ሲመሰረት በድጋሚ ዋስትና እንደሚጠይቁም ተናግረዋል። ጠበቆቹ ተጠርጣሪው ወደ ሁለት ወር ገደማ በመታሰራቸው ክርክሩ እንዲጀመር ያቀረቡትንም ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ሳይቀበለው ቀርቷል።

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም ደንበኛቸውን በሳምንት ሁለት ቀናት (ረቡዕ እና ዓርብ) ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል። ዶ/ር መረራ ጉዲና አሁንም ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት አልተፈቀደላቸውም። የዶ/ር መረራ ጉዲና የምርመራ ሒደት እስከ አራት ወራት ሊዘልቅ ቢችልም ጠበቃቸው በድጋሚ ተቃውሟቸውን እንደሚገልጡ ተናግረዋል። መርማሪ ፖሊስ በተደጋጋሚ ሌላ ቀነ-ቀጠሮ ሊጠይቅ ይችላል የሚል ስጋት ያላቸው ዶ/ር ያዕቆብ መረጃ የማሰባሰቡ ሒደት እስካሁን መጠናቀቅ ነበረበት ብለዋል። ዛሬ ያስቻለው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የዶ/ር መረራ ጉዲናን ጉዳይ  ለመጪው የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ.ም. ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል። 


እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ