1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመናዉያን የሞቱበት የኢስታምቡሉ ጥቃት

ረቡዕ፣ ጥር 4 2008

ትናንት ኢስታምቡል ቱርክ ላይ ከደረሰዉ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ጋር በተገናኘ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የቱርክ ፖሊስ አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/1Hca4
Türkei De Maiziere und Efkan Ala PK zum gestrigen Anschlag in Istanbul
ምስል Reuters/M. Sezer

[No title]

የሀገር ጎብኚዎች መነኻሪያ በሆነችዉ በታሪካዊቱ ኢስታንቡል ከተማ የ10 ጀርመናዉያን ጎብኚዎችን ህይወት የቀጠፈዉን ጥቃት ያደረሰዉ ራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለዉ ፅንፈኛ ቡድን አባል የሆነ የ28 ዓመት ሶርያዉ መሆኑም ተገልጿል። ትናንት በደረሰዉ ጥቃት ከሞቱት ሌላ 15 ሰዎችም ተጎድተዋል። አብዛኞቹ ጀርመናዉያን ሲሆኑ የኖርዌይ ዜጎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል። የቱርክ የሀገር ዉስጥ ሚኒስትር ኢፍካን አላ ማንነቱ በዝርዝር ባይገለፅም ከጥቃቱ ጋር በተገናኘ አንድ ግለሰብ ትናንት ማምሻዉን መያዙን ዛሬ አስታዉቀዋል። ጉዳዩን በቅርበት ለመመርመር ወደዚያ የተጓዙት የጀርመን የሀገር ዉስጥ ሚኒስትር ቶማስ ደሚዜር፤ ምንም እንኳን የጥቃቱ ሰለባዎች ጀርመናዉያን ቢሆኑም፤ እነሱ ላይ ብቻ አደጋዉ እንዳነጣጠረ የሚያሳምን ነገር አለመኖሩን ተናግረዋል። በዚህ ምክንያትም ወደቱርክ ለመጓዝ ያቀዱ ጀርመናዉያን ሃሳባቸዉን መለወጥ እንደማያስፈልጋቸዉ አመልክተዋል። አንድ የታወቀ የጀርመን አስጎብኚ ድርጅት በበኩሉ ወደቱርክ ለመጓዝ የተመዘገቡ ደንበኞቹ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ የጉዞ አቅጣጫቸዉን ወደሌሎች ሃገራት መቀየር እንደሚችሉ ይፋ አድርጓል። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

Türkei Istanbul Altstadt Sultanahmet Hagia Sophia Moschee
ምስል Getty Images/D. Cannon

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ