1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመናዊ እና ጥቁርነት

ቅዳሜ፣ መስከረም 12 2005

«ጀርመናዊ ነን ግን ማህበረሰቡ እንደ ጀርመናዊ አይመለከተንም» ይላሉ አንዳንድ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸውና ጠይም የሆኑ ከነጭ እና ጥቁር የተወለዱ ጀርመናዊያን።

https://p.dw.com/p/16C12
Deutsche und türkische weibliche Fußballfans feiern am Mittwoch (25.06.2008) vor der Kölnarena in Köln beim Public Viewing. Die deutsche Fußball-Nationalmannschaft trifft im EM-Halbfinale auf die Türkei. Foto: Rolf Vennenbernd +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/dpa

ራሳቸውን «አፍሮ ዶይቸ» ብለው የሚጠሩ አፍሪቃዊ ዝርያ ያላቸው ጀርመናዊያን አብዛኛውን ጊዜ እንደ ማንኛውም ጀርመናዊ እንደማይታዩ ይናገራሉ። ጀርመናዊነትና ጥቁርነት በአንድላይ አሁንም ለማህበረሰቡ እንግዳ ነው። ይሁንና 500 ሺ የሚሆኑ ከአፍሪቃውያን እና ከጀርመናዊያን የተወለዱ ጀርመናዊያን በጀርመን ሀገር ይኖራሉ። ከነዚህ አፍሮ ዶይቸ በመባል ከሚታወቁት መካከል ሁለቱ የዛሬው ዝግጅት እንግዶቻችን ናቸው።

ቪንሰት ባባቦኡቲላቦ ከኮንጎላዊ አባቱ እና ከጀርመናዊ እናቱ ነው የተወለደው። የ 23 አመቱ ወጣት ተወልዶ ያደገው በበርሊን ከተማ ነው። አሁን የሙዚቃ ትምንህርትን በዮንቨርስቲ ደረጃ እያጠና ይገኛል። ጀርመናዊ ነው፤ ይሁንና ጀርመናዊ እንዳልሆነ ነው የሚሰማው። «ሁልጊዜ ከውጭ ሀገር ዜጎች ተርታ ነው የምመደበው። የሚያናድድ እኮ ነው። እኔ የውጭ ሀገር ዜጋ አይደለሁም። እዚህ ነው የተወለድኩት፤ የውጭ ሀገር ዜጋ ልሆን አልችልም። ይህ ነው ብዙውን ጊዜ እጅጉን የሚያስቆጣኝ።»

***Achtung: Nur zur mit Vincent Bababoutilabo abgesprochenen Berichterstattung verwenden!*** Der 23-jährige Musikstudent Vincent Bababoutilabo ist der Sohn eines Kongolesen und einer Deutschen. Er ist in Berlin geboren und aufgewachsen. Copyright: privat Schriftliche Einverständniserklärung per mail durch DW/Katrin Matthaei geliefert. undatiert, eingestellt September 2012
ቪንሰት ባባቦኡቲላቦምስል privat

ሰዎች ቪንሰትን እንደ የውጭ ሀገር ዜጋ የተቀበሉበትን ጊዜ ቢቆጥር መጨረሻ እንደሌለው ይናገራል። ቅርብ ጊዜ የገጠመውን እንደ ምሳሌ ይናገራል። ወደሚማርበት ዮንቨርሲቲ ሄዶ በር ጠባቂውን ዋሽንት መለማመጃው ክፍል የት እንደሆነ ሲጠይቃቸው፤ ቋንቋ አይችል ይሆናል ብለው በማሰባቸው እንዲገባው ረጋ ብለው ቃል እየመረጡ አስረዱኝ ይላል ቪንሰት። አልፎ አልፎም ጀርመንኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ የሚሉትና የሚያወድሱት እንዳሉትም ይናገራል። ሌሎች ደግሞ ከየት አገር ነው የመጣኸው እያሉ ይጠይቁታል።
«ጀርመናዊ ነኝ ስላቸው ሁልጊዜ አባትህ ወይንም አያትህ ከየት ሀገር ናቸው የሚል ጥያቄ ይቀርብልኛል። ይህ ጥያቄ አይ ሙሉ ጀርመን አይደለሁም እስክል ድረስ ይቀጥላል። ምክንያቱም ጀርመን ውስጥ ሰው በደሙ ነው የሚገለፀው መሰል።»


ለረጅም ጊዜ ቪንሰት ማንነቱን ሲጠይቅ ቆይቷል። ነገር ግን ማንነቱን በጀርመንም ሆነ በኮንጎ ጎኑ ሊያገኝ አልቻለም። አንድ ቀን ይላል ቪንሰት። አንድ ጥቁር ጓደኛዬ እጇን ከእጄ ጎን አድርጋ ካስተያየች በኋላ በደንብ ጥቁር እንዳልሆንኩ ገለፀችልኝ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ቪንሰት ሌሎች ስለሱ ማንነት እንዲነግሩት በፍፁም እድል አልሰጥም ባይ ሆኗል። በመጨረሻ ቪንሰት የደረሰው ውሳኔ ፤ ጥቁር ወይንም ነጭ ሳልሆን ሁለቱንም ነኝ የሚል ነው።
« አሁን ገና ነው ራሴን በትክክል ያወቅሁ። ይኼውም። እኔ፤ እኔ ነኝ በማለት። ውስጤ ሁለት ገፅታዎች አሉ። በዚህ ደግሞ ልኮራ ይገባል። ስለሆነም አንድ ጎን መያዝ የለብኝም።»
የ 20 አመቷ ጀርመን ሴኔጋላዊ እይታ ግን ከመጀመሪያው አንስቶ ከ ቪንሰት የተለየ ነበር። ንዴላ ባ የአፍሪካንስቲክ ተማሪ ነች። ለማንነት ጥያቄዋ ገና ድሮ ነው መልስ ያገኘችለት። ተወልዳ ያደገችው እዚሁ ቦን አቅራቢያ በምትገኘው የኮሎኝ ከተማ ነው። የአውሮፓዊነትን እና የአፍሪቃዊነትን አስተሳሰብ ይዛ እንዳደገች ትገልፃለች። ትምህርት ቤት ሲዘጋ በየአመቱ ከቤተሰቦቿ ጋ ወደ ሴኔጋል ይጓዙ ነበር።የ 11 ኛ ክፍል ትምህርቷን በሴኔጋል መዲና ዳካር ነው የጨረሰችው። አሁን ድረስ ከአባቷ ጋ በየጊዜው የሴኔጋል ባህላዊ ምግብ ትሰራለች።

Beitrag Afrodeutsche - Fremd im eigenen Land: Ndella Ba. Bild aus dem Privatarchiv, Undatierte Aufnahme, Eingestellt 12.09.2012
ንዴላ ባምስል Ndella Ba

« የአፍሪቃዊ ባህሌ ሁሌ አብሮኝ አለ። ያደጉት ከአፍሮ ጀርመናዊ ጓደኞቼ ጋር ነው። አባቴ በርካታ አፍሪቃዊ ጓደኞቹን ወደቤት ይጋብዝ ነበር። በዚህ የተነሳ የአፍሪቃዊ ማንነቴን አንግቼው ነበርና መፈለግ አልነበረብኝም። ጀርመናዊነቴ ደግሞ አብሮኝ የኖረ ነው። ጀርመን ሀገር ነው ያደግኩት። ስለሆነም ደንበኛ ጀርመን ነኝ ማለት እችላለሁ። በበኩሌ ለሁለቱ ባህሌ ጥሩ ሚዛን አግኝቼለታለሁ ብዬ አምናለሁ።»
ቢሆንም ንዴላ በዕለት ከለት ኑሮዋ ሰዎች በቆዳ ቀለሟ የተነሳ እንደ ጀርመናዊ እንደማይመለከቷት ታዝባለች። ይህ ግን እምብዛም አያሳስባትም። እንዳውም እንደዚህ አይነት ሰዎች ሲገጥሟት ጀርመናዊ መሆን እና ጥቁር የቆዳ ቀለም አብሮ ሊሄድ እንደሚችል ታብራራላቸዋለች። ጀርመንኛ አቀላጥፋ በመናገሯም፤ ሊያወድሷት እንደማይገባ ትነግራቸዋለች።

« እኔ ዘና ብዬ ነው የማየው። ጀርመናዊ እንደሆንኩ እና ጀርመንኛ አፍ የፈታሁበት ቋንቋ እንደሆነ ለመግለፅ ምንም ችግር የለብኝም ። እንደሚመስለኝ አለማወቅ ነው ችግሩ፤ ሰዎች ደግሞ ግልፅ እንዲሆንላቸው ይፈልጋሉ። አብዛኛውን ጊዜ በመናደድ ፋንታ ያስቀኛል።»
እንዲያም ሆኖ የምትሰጠው ማብራሪያ ውጤት እንደሚያሳይ እና ጀርመናዊ መሆንና ጥቁር የቆዳ ቀለም መያዝ ማይፃረር ክስተት እንደሆነ ሰዎች ይረዳሉ ብላ ተስፋ ታደርጋለች። ማህበረሰቡ ለምን አልተቀበላቸውም? ለነዚህ ወጣቶችስ ምን አይነት አስተዋጽዎ ይኖረዋል? ለዶክተር መኮንን ሽፈራው አንዳንድ ጥያቄቆች አንስተንላቸዋል።
ዶክተር መኮንን ከ20 አመታት በፊት የመሰረቱት የባብል ኤ ፋው ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ናቸው። ድርጅቱ በውጭ ዜዎች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን መቋቋም የሚቻልበትን መንገድ ነድፎ እስካሁን ይንቀሳቀሳል።
የተለያዩ ባለድርሻዎች ፣ መንግስት ፣ በስሪያ ቤቶች፣ ማህበረሰቡ ምን ማድረግ ይገባቸዋል? ከዝግጅቱ ያገኙታል።


ልደት አበበ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ