ጀርመናውያንና ሳይንሳዊ ያልሆኑ ባህላዊ እምነቶቻቸው፣
ረቡዕ፣ ግንቦት 4 2002ማስታወቂያ
ሰው፣ በተለይ ለማያውቀው፣ ተመራምሮም ገና ምላሹን ላላገኘለት ጉዳይ፣ የራሱን ግምትም ሆነ መላ-ምት በማስቀመጥ፣ አመክንዮ በሌላቸው የተለያዩ ልማዳዊ እምነቶችን የመቀበል አዝማሚያ ይታይበታል።
አስማት፣ ጥንቆላ፣ ሳይንሳዊ መረጃ የሌለው እምነት ፣ እነዚህ ሁሉ፣ እስከዛሬ ድረስ በዕለት-ተዕለት ባህላዊ እንቅሥቃሤ ቦታ አላጡም። ሰይጣን፣ ርኩሳን መናፍስት፣ መላእክትና ተረታዊ ታሪኮች፣ የሰው፣ የማይወገዱ የባህሉ አካላት ሆነው ቀጥለዋል። መጥፎም ሆነ ጥሩ ገድ፣ በሚባሉ ምልክቶች የማመኑና የመጠራጠሩ አባዜ ፣ የሥነ-ልቡና ጠበብት እንደሚሉት፣ የሰው ልጅ ያለመርካት ውጤት ሲሆን፣ ይህ ራሱ ከራሱ፣ ከሰው ፍጥረትና አብሮ ከመኖር ባህል ጋር ተሣሥረው የዘለቁ ናቸው።
ተክሌ የኋላ
ሒሩት መለሰ፣