1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመንና የአቶም ሐይል ማመንጫዎችዋ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 6 2003

በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የፉኩሺማ የኒዩክልር ኃይል ማመንጫ የደረሰበት ያልታሰበ ጉዳት አደገኛ የአቶም ጨረር እንዲያፈተልክ ሊያደርግ መቻሉና ወደፊትም የሚያሳድረው ተፅዕኖ ሁሉንም በየሀገሩ እያነጋገረ ነው ።

https://p.dw.com/p/R9Sp
ምስል picture-alliance/dpa

ጉዱዩ የአቶም ኃይል ማመንጫ ማዕካላቷን ዕድሜ ለማራዘም በወሰነችው በጀርመን በእጅጉ እያከራከረ ነው ። የጀርመንን የኒዩክለር ኃይል ማመንጫዎችን ለመዝጋት ከዚህ ቀደም የተያዘው ዕቅድ መቀልበስ የለበትም ሲሉ በወቅቱ የተከራከሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቃውሞአቸውን አሁን ይበልጥ እያስተጋቡ ነው ። መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልም ሳይቀደሙ ፣ እጎአ በ 2010በመስከረም ወር የተላለፈውን የአቶም

Deutschland Atomkraft Proteste Japan Atomkraftwerke Mahnwache
ምስል AP

ኃይል ማዕከላት መክሰሚያ ጊዜ ማራዘሚያ ውሳኔ እንደገና እንደሚጠና አስታውቀዋል ። በዚህ ምክንያትም ቢያንስ ሰባት አሮጌ የአቶም ኃይል ማመንጫ አውታሮች ለጊዜው እንዲዘጉ ተደርጓል ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን በፉኩሽማው የአቶም ኃይል ማመንጫ ላይ በደረሰው ጉዳት መንስኤ ጀርመን ውስጥ የተነሳውን ክርክርና መንግስት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ይመለከታል ።

ሂሩት መለሰ
ነጋሸ መሐመድ