1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን ለስደተኞች የምትሰጠው ገንዘብ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 18 2004

የጀርመን ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ፣ መንግሥት ጀርመን ለሚኖሩ ስደተኞች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጎማ ከፍ እንዲያደርግ አዟል ። የፍርድቤቱ ውሳኔ ጥያቄውን ደጋግመው ያቀርቡ የነበሩ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶችንና

https://p.dw.com/p/15dvt
ARCHIV - Asylbewerberinnen sitzen am 22.09.2010 in der Zentralen Aufnahmeeinrichtung des Landes für Flüchtlinge in Nostorf/Horst bei Boizenburg auf einer Straße. Das Bundesverfassungsgericht entscheidet am 18.07.2012 darüber, ob Flüchtlinge und andere Menschen ohne dauerhaftes Aufenthaltsrecht mehr Geld vom Staat bekommen müssen. Seit 1993 sind die Beträge nach dem Asylbewerberleistungsgesetz nicht erhöht worden. Foto: Jens Büttner dpa +++(c) dpa - Bildfunk+++
ምስል picture-alliance/dpa


የጀርመን ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባለፈው ሳምንት ፣ መንግሥት ጀርመን ለሚኖሩ ስደተኞች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጎማ ከፍ እንዲያደርግ አዟል ። የፍርድቤቱ ውሳኔ ጥያቄውን ደጋግመው ያቀርቡ የነበሩ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶችንና ተገን ጠያቂዎችን አስደስቷል ። ሆኖም የትዕዛዙ አፈፃፀም እያነጋገረ ነው ።
እስካሁን የሚሰራበት የጀርመን የተገን ጠያቂዎች አያያዝ ህግ እጎአ በ1993 የወጣ ህግ ነው ። በወቅቱ ስደተኞች በብዛት ጎረፉ ተብሎ አለአግባብ ተገን የሚጠይቁ ሰዎችን ለመግታት ሲባል የወጣው ይኽው ህግ ወጪን ለመቀንስ ታስቦ የተወሰደም እርምጃ ነበር ። በህጉ መሰረት ስደተኞች ተገን የጠየቁበት ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶች ይሰጣቸው ነበር ። ይህን አገልግሎት በመስጠትም ሆነ ተግባር ላይ በማዋል ወጪውንም በመሸፈን ህጉ ሃላፊነቱን ለፌደራል ክፍላተ ሃገር ነው የሰጠው ። ውሎ አድሮ ግን በአንዳንድ ፌደራል ክፍላተ ሃገር የገንዘብ ክፍያው እንዲቀር ተደረገ ። በተለያ የባየርን ፊደራል ክፍለ ሃገር እንዲሁ አግልግሎት በመስጠት ላይ ብቻ ነበር ያተኮረችው ። ከዛሬ 12 ዓመት በፊት ወደ ጀርመን የተሰደደውና በአሁኑ ጊዜ Proasyl በተባለው ድርጅት የወጣቶች ኮሚቴ አባል ወጣት ፈለቀ ባህሩ በጥገኝነት ጠያቂነት በቆየበት በባየርን ወይም በባባቫርያ ፌደራዊ ክፍለ ሃገር የስደተኞች አያያዝ ምን እንደሚመስል ከሌላ አካባቢ ጋራ በማነፃፀር ያስረዳል ።  

ከበርሊን ወጣ ብሎ በሚገኝ ሥፍራ ያሉ ያሉ ስደተኞች ደግሞ 220 ዩሮ ነው እስከዛሬ የሚያገኙት ። ይህ ብዙ ገንዘብ ይመስል ይሆናል ሆኖም ኑሮ ውድ በሆነበት በጀርመን በቂ አይደለም ። አብዛኛዎቹ ደግሞ የምግብ ራሽን ነው የሚያገኙት ። ራሽኑ የሚሰራውም በተወሰኑና ውድ በሆኑ የምግብ መሸጫዎች ሱቆች ብቻ ነው ። በዚህ ስፍራ ለዓመታት የኖሩት ከኬንያና ከካሜሩን የመጡት ፌስቱስና ቶኒ እንደሚሉት በዚህ ምክንያት ረከስ ወዳሉት ሱቆች እንኳን መሄድ አይችሉም ።
«ካይሰርስ እጅግ በጣም ውድ ሱቅ ነው ። ከጓሯችን ኔቶ አለ ግን ኔቶ መሄድ አንችልም »
የሰጣቸው የምግብ ራሽን ወረቀት ላይ  ፈርመው መታወቂያቸውን አሳይተው ነው አገልግሎቱን የሚያገኙት ። ይህ ጊዜ ስለሚወስድ ሌሎች ገበያተኞች ያመናጭቋቸዋል ። በዚህ የተነሳም እየተማረሩ ሞት የሚመኙበት ጊዜም አለ ። እነዚህ መሥራት የማይፈቀድላቸው ተገን ጠያቂዎች በተለያዩ የጀርመን ፊደራል ክፍለ ግዛት አያያዛቸው ቢለያይም ከሚሰጣቸው መሠረታዊው አግልግሎት ሌላ ሲታመሙ በርግዝና ውቅትም ሆነ ልጅ ሲወለዱ ተጨማሪ አገልግሎት ያገኛሉ። ካርልስሩኽ የሚገኘው የጀርመን ህገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የተገን ጠያቂዎች ገቢ አነስተኛነት የሚያመለክቱ 2 ክሶች ከቀረቡለት በኋላ ባለፈው ረብዕ ባሳለፈው ብይን የሚሰጣቸው መሰረታዊ አግልግሎት በተጨባጭ ሁኔታ ተገንዝቦ በቂ አልነበረም ከሚል መደምደምያ ላይ ደርሷል ። የፍርድ ቤቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ፌርዲናንድ ኪርሽሆፍ እንደተናገሩት ስደተኞች እስካሁን ይሰጣቸው የነበረው ገንዘብ በሃገሪቱ መሰረታዊ ህግ የተቀመጠውን መስፈርት አላሟላም ።
« ሴኔቱ የተገን ጠያቂዎችን በሚመለከተው ህግ የሚከፈለው ገንዘብ መሰረታዊ ህገ መንግሥት በሚጠይቀው መሰረት ሰብዓዊ ክብርን የሚጠብቅ ድጎማ እልተሰጠም ሲል ወስኗል ። ህግ አውጭዎች ያለ አንዳች ማመንታት ህገ መንግሥቱን ተመርኩዘው አዲስ ደንብ ማውጣት ይኖርባቸዋል ። »

Baden-Wuerttemberg/ Der Vorsitzende Richter des Ersten Senats des Bundesverfassungsgerichts (BVerfG), Ferdinand Kirchhof, spricht am Mittwoch (18.07.12) im Rahmen der Urteilsverkuendung in Sachen "Asylbewerberleistungsgesetz/Grundleistungen" im Gerichtssaal des Bundesverfassungsgerichts in Karlsruhe. Die staatlichen Geldleistungen fuer Asylbewerber in Deutschland sind zu niedrig und verstossen damit gegen das Grundgesetz. Das hat das Bundesverfassungsgericht in Karlsruhe am Mittwoch entschieden. Die entsprechenden Regelungen des Asylbewerberleistungsgesetzes verletzten das Grundrecht auf Gewaehrleistung eines menschenwuerdigen Existenzminimums. (zu dapd-Text) Foto: Ronald Wittek/dapd
ምስል dapd


በዚሁ ውሳኔ መሰረት ተገነ ጠያቂዎች እስከ ዛሪ ያገኙት የነበረው 240 ዩሮ ወደ 336 ዩሮ ከፍ ይላል ። ይህ የገንዘብ ጭማሪም በስደተኞች መብት ተሟጋቾች ዘንድ ተወድሷል ። ይህን ጥያቄ በተደጋጋሚ ሲያነሳ የነበረው የProasyl የወጣቶች ኮሚቴ አባልና እጎአ የ2009 ዓም የ ድርጅቱ የሰብዓዊ መብት ተሸላሚ ፈለቀ ባህሩ ውሳኔው አስደሰቶታል ። ሆኖም አሁንም አንዳንድ ስጋቶች አሉት ።
ድምፅ
አዲስ ደንብ እስኪወጣ ድረስ የተገን ጠያቂዎችን ጉዳይ ከሚመለከተው ህግ አኳያ ዳኞች ህርትስ ፍየር ሃርትስ 4  ማለትም በጌርሃርድ ሽሮደር አስተዳደር ዘመን ሥራ ላጡ ወገኖች ድጎማ የሚሰጥበት ደንብ ጋር የሚዛመድ መመሪያ ነው ያወጡት ። በዚህ ደንብ መሰረት ለጀርመናውያንም ሆነ ለውጭ ሃገር ተወላጆች የሚሰጠው የመጨረሻ ዝቅተኛ ክፍያ እኩል ነው ። ቀደም ባለው ጊዜ ይኽው እጅግ ዝቅተኛ ክፍያ ይሰጥ የነበረው ወደ ጀርመን የመፍለስ ዝንባሌ ወይም ፍላጎት ያላቸውን ስደተኞችን ተስፋ ለማስቆረጥ ነበር ። በአሁኑ ሰዓት 130 ሺህ ገደማ የሚሆኑ የተለያየ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች ተገቢውን የገንዘብ ድጋፍና አገልግሎትት በማግኘት ላይ ናቸው  ። ፍርድ ቤቱ እንደደረሰበት እነዚህ ከ6 ዓመት  በላይ ጀርመን የተቀመጡ ናቸው ። ከመካከላቸው 65 ሺሁ የጀርመን የሥራ ሚኒስቴር እንዳለው ተገን የጠየቁበት ጉዳይ በመጣራት ላይ ነው ከነዚህም በተጨማሪ ከጦርነት ሸሽተው ተሰደው የገቡና በየጊዜው በሚታደስ ጊዜያዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሚቆዩም አሉ ። ጀርመን የሚኖሩ አንዳንድ ጥገኝነት ጠያቂዎች እንደሚሉት ከገንዘቡ ማነስ ሌላ የአኗኗራቸው ሁኔታም ሊለወጥ ይገባዋል ።ቶኒና ፌስቱስ በየጊዜው በሚታደስ የተገደበ የመቆያ ፈቃድ ሲኖሩ ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል ። በተጠለሉበት ቦታ በአንድ ክፍል ውስጥ እስከ 5 ስደተኞች ድረስ በጋራ ይኖራሉ ። እስከ መቼ በዚህ ስፍራ እንደሚቆዩ የማያውቁ 400 ያህል ስደተኞች ይገኛሉ ። ፌስቱስ የጋራው ኑሮ አስመርሮታል ።

«በአንድ ክፍል ውስጥ ስትኖር አንዳንድ ነገሮችን ለብቻህ ማድረግ ትፈልግ ይሆናል ።ከሌላ አገር የመጣ ቤተሰብህ ያልሆነ ሰው ፊት ለመልበስ ትገደዳለህ ህይወትህ ክብር አይኖረውም ። ሰው ሳያይህ የምታደርገው ነገር አይኖርም ። »
ለተገን ጠያቂዎች የሚሰጠው የገንዘብ ድጎማ እንዲጨመር የተላለፈው ውሳኔ በአብዛናዎቹ የጀርመን ፖለቲከኞች ዘንድ እንደ አንድ ትልቅ እርምጃ ተወስዷል ። እርምጃው ስደተኞች ያሉባቸውን ሌሎች ችግሮች ለመፍታት ለሚደረጉ ጥረቶችም ተስፋ ሰጭ ሆኖ ነው የታየ ው ።
በአውሮፓ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት መረጃ መሰረት ጀርመን እጎአ በ2011 ከአውሮፓ ሃገራት በተቀበለቻቸው ስደተኞች ብዛት ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ። በዚሁ ዓመት ጀርመን 13 ሺህ ስደተኞችን ተቀብላለች

ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ

Vorwiegend rumänische Asylbewerber laufen am 25.06.1992 in Rostock-Lichtenhagen zu bereitgestellten Bussen. Tagelang campierten im Juni 1992 vor der zentralen Asylanten-Aufnahmestelle (ZAST) für Mecklenburg-Vorpommern in Rostock-Lichtenhagen bis zu 130 Asylbewerber unter Balkonnischen oder freiem Himmel, weil das Heim mit 300 ausländischen Bürgern bereits hoffnungslos überfüllt war. Am 25.06.1992 endlich wurden sie mit Bussen in ein anderes Heim gebracht. Foto: Bernd Wüstneck
ምስል picture-alliance/ZB
ARCHIV - Ein junger Asylsuchender aus Malawi sitzt am 12.12.2011 in Frankfurt am Main in der hessischen Erstaufnahmeinrichtung für Flüchtlinge am Frankfurter Flughafen. Der hessische Sozialminister Grüttner besuchte an diesem Tag das Haus, das nach Angaben des Ministeriums bundes- und europaweit als Modelleinrichtung gilt. Mehrere Tausend minderjährige Flüchtlinge leben in Deutschland - ganz ohne Familie. Viele waren jahrelang unterwegs und haben Schreckliches erlebt. (Zu dpa KORR "Mutterseelen allein - Minderjährige Flüchtlinge in Deutschland"). Foto: Frank Rumpenhorst dpa/lhe
ምስል picture alliance/dpa