1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፤ መራሂተ መንግሥቷ ምሥጋና አቀረቡ

እሑድ፣ ሚያዝያ 25 2007

በባቫርያ ግዛት የሚገኘዉ « ዳሃዉ» የተሰኘዉ የናዚ ማጎርያ ጣብያ ነፃ የሆነበት 70 ኛ ዓመት ዛሬ በማስታወስና በፀሎትሥነ-ስርዓት ታስቦ ዋለ። በዝግጅቱ ላይ መራሒተ መንግሥት አጌላ ሜርክልን ጨምሮ 130 ከማጎርያዉ ጣብያ በሕይወት የተረፉ ሰዎችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተካፋይ ነበሩ።

https://p.dw.com/p/1FJPn
Deutschland 70. Jahrestag der Befreiung des KZ Dachau
ምስል Bundesregierung/Bergmann/dpa

መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፤ በተለይ ከ«ዳሃዉ» ማጎርያ ጣብያ በሕይወት የተረፉት ሰዎች ስለሚሰጡት ምሥክርነት አመስግነዋል። «ዳሃዉ » የተሰኘዉ የናዚ ማጎርያ ጣብያ በጎርጎሪዮሳውያኑ አቆጣጠር 1933 ዓ.ም ተመስርቶ ናዚ በመንበረ-ሥልጣኑ በቆየበት 12 ዓመታት ዘልቆ የቆየ ማጎርያ ጣብያ መሆኑ ይታወቃል። በጎርጎረሳዉያኑ ሚያዝያ 29፤ 1945 ዓ,ም የዩኤስ አሜሪካ ወታደሮች ማጎርያ ጣብያዉን ነፃ ሲያስለቅቁ፤ 32 ሺህ ሰዎች ከሞት መትረፋቸዉ ይታወቃል። እንደ ጀርመን ሙዚዬሞች የታሪክ ማኅደር ከሆነ በዳሃው የናዚ ማጎሪያ በወቅቱ 41 500 ግድም እሥረኞች መገደላቸው ይታወቃል። በ«ዳሃዉ» ማጎሪያ ጣቢያ በናዚ ዘመን ከመላው አውሮጳ ቁጥራቸው 200 000 የሚገመት ሰዎች በመያዝ ታጉረው እንደነበር ይነገራል።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ