1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፣ ስደተኞች እና የመራሒተ መንግሥቷ አቋም

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 28 2008

ቢያንስ የሰው አመለካከት ለሁለት ተከፍሎአል፡፡አሁንም ቢሆን አንዳዶቹ „…ከፊታችን የተደቀነውን ችግር እንፈታዋለን፣እንወጠዋለን“ ብለው የሚያምኑ ናቸው፡፡ ሌሎቹ ክፍሎች ደግሞ ይህን በጥርጣሬ ዓይን ይመለከታሉ፡፡

https://p.dw.com/p/1Just
Infografik Wie verändert Merkels Flüchtlingspolitik Deutschland? Terror Englisch

ከዚያም አልፈው እንዲያውም እነሱ፣ መራሂተ መንግሥትዋን ይህን እሳቸው ያለፈው ዓመት„….እንወጣዋልን“ ያሉትን ቃል ፊት ለፊት አሁን ይቃወማሉ፤ይተቻሉም፡፡ በጀርመን አገር ውስጥ ነገሮች እየተቀያየሩን እየተለዋወጡ እንደመጡ እዚያ እና እዚህ የሚታዩ ፍንጮች በቂ ምስክሮች ናቸው፡፡እንግዲህ በአስደንጋጩ ዜና እና በአሳዛኙ አካሄድ እንጀምር፡፡

ዘረኛነት በአገሪቱ እየተጠናከረ መጥቶአል፡፡

Deutschland CDU Parteitag - Abstimmung Flüchtlingspolitik
ምስል Reuters/K. Pfaffenbach

ተገን ፈላጊ ስደተኞች፣ አገርና ድንበር አቆራርጠው እዚህ ከመድረሳቸው በፊት፣ ዕጣ ዕድሉ ጨልሞበት ወደታች አቆልቁሎ በመራጩ ሕዝብ ዘንድ እዚህ ጀርመን አገር ምንም ያህል ድጋፍ ያልነበረው አንድ የቀኝ አክራሪ „ AfD“ - ማለትም፣ „…አማራጭ ኃይል ለጀርመን“ ብሎ ራሱን የሚጠራው የፖለቲካ ፓርቲ ፣ አሁን „…በስደተኞች ተወረርን „ በሚለው የማሥፈራሪያ ቅስቀሳው፣ ብዙ ተከታዮችን በቀላሉ ለመሰብሰብ ችሎአል፡፡ ሁኔታውን፣ይህ ድርጅት በደንብ ተጠቀሞበታል፡፡

የሰውን አስተሳሰብና አመለካከታት እዚህ በየጊዜው ተከታትለው የሚያጠኑ የምርምር ጣቢያዎች እንደሚሉት ከሆነ ደግሞ፣ ይህ ፓርቲ „ ኤ ኤፍ ዲ“ በመላው ጀርመን ምርጫ በቅርቡ ቢካሄድ ከመቶ አሥራ አምስት ድምጽ አግኝቶ ሸንጎ ውስጥ ለመግባት ችሎታ እንዳለው እነሱ ጠይቀው በአገኙት መረጃዎች አረጋግጠዋል፡፡

በአለፈው ጊዜ በተካሄደውም የምርጫ ወራት፣ይህ ድርጅት እንኳን ከመቶ አሥራ አምስት ድምጽ ማግኘት ቀርቶ ፣የሚጠበቅበትን አምስት ከመቶ ድምጽ በቀላሉ መሰብሰብ አቅቶት ከሸንጎው በር ይህ ድርጅት ተመልሶአል፡፡ ይህ አይረሳም!

ጊዜው ተቀይሮ ግን አሁን ለድርጅቱ አመቺ የሆነ ሰዓት የመጣ ይመስላል፡፡

በውጭ አገር ሰዎች የሚሰነዘረው የጥላቻ ቃላትና ፣እዚያና እዚህ የሚታየው ዝንባሌ ፣እራሱ በአገሪቱ ላይ የሚታየው መንፈስ፣ የአደባባይ ሚስጢር በብዙ ቦታ ነገሩን አድርጎታአል፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ እዚህ እንደሚሉት የመጠጥና የራት ግብዣ አርዕስትም ሁኖ፣ብዙ ሰው ሳይፈራ ፣ፊት ለፊት የሚነጋገርበት ጉዳይ ሁኖአል፡፡

ያም ሁኖ ይህ!... አሁን እዚህ ስደተኞቹ ከመጡ ወዲህ ብቅ ያለውን አዲስ ሁኔታና ችግር፣ ከሌሎቹ የአዉሮጳ አገሮች ጋር ሲነጻጽርና ሲወዳደር በጣም ዝቅተኛ ቦታ የያዘ ነው፡፡ አወዳድሮ ተገቢውን ቦታም ማስያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ ለምሳሌ በፈረንሣይና በቡልጋሪያ የሚንቀሳቀሱ የቀኝ አክራሪ ድርጅቶች በምርጫ ከመቶ ሃያ ድምጽ በላይበአካባቢያቸው አግኝተው፣እነሱ ሸንጎው ውስጥ ገብተው፣ ወንበራቸውን ይዘው እዚያ እነሱ የልባቸውን መናገር ጀምረዋል፡፡

በፖላንድና በሓንጋሪ ደግሞ ተመሣሣይ አላማ ያላቸው ድርጅቶች ከዚያ አልፈው በብዙሃኑ ሕዝብ ተመርጠው፣ ወንበሩን ተረከብው መንግሥት መሥርተው ፣አገራቸውን እዚያ ሕግ እያወጡ ማስተዳደር ከጀመሩ ጊዜው ሰንበት ብሎአል፡፡ በሌላ አካባቢ በታላቁዋ ብርታኒያ ለየት ያለ ሥዕል እዚያ እናያለን፡፡

በዚህ በውጭ አገር ሰዎች ጥላቻ ላይ በተመሠረተው ፖለቲካቸው „UKIP“- ተብሎ እራሱን በብርታኒያ የሚጠራው ድርጅት፣ እሱ እራሱ በመጀመሪያ በለኮሰው ቅስቀሳው፣ ሕዝቡን የሁዋላ ሁዋላ ጎትጉቶ ፣ የብርታኒያ መንግሥት የአዉሮጳን አንድነት ማህበረሰብ ለቆ እንዲወጣም ይህ ድርጅት፣ያልተጠበቀ ሚና እዚያ ሊጫወት ችሎአል፡፡

ከዚህ አንጻር፣ በጀርመን አገር የሚገኙት የቀኝ አክራሪዎች በምንም ዓይነት ምሥራቅ አዉሮጳ ውስጥ ከበቀሉት የቀኝ ዘመምተኞች ጋር በቁጥርም ሆነ በጥንካሬአቸውም ከእነሱ ጋር አይወዳደሩም፡፡ አሁንም ቢሆን በጀርመን አገር፣አክራሪዎቹ ሳይሆኑ፣ የጀርመን መንግሥት እንደ አለፉት ጊዜያት፣ የተረጋጋ እና የሰከነ የፖለቲካ እርምጃውን በኃላፊነት ላይ የተቀመጡት ፖለቲከኞች አጥንተውና አመዛዝነው የሚወሰዱበት አገር ነው፡፡

እርግጥ ኑዋሪው ሕዝብ በመራሂተ መንግስትዋ ላይ ያለው አመለካከት እንደ አለፉት ጊዜያት ሳይሆን አሁን ተቀይሮአል፡፡ ይህ አይካድም፡፡እንደ አለፉት አመታት ዘነድሮ፣ መራሂተ መንግሥትዋ ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅ አይደሉም፡፡መገመት እንደሚቻለው የደጋፊዎቻቸው ቁጥር በአገር ደረጃ ቀንሶአል፡፡ ይህም ምክንያት አለው፡፡

Angela Merkel mit roter Handtasche
ምስል picture-alliance/dpa/B.v.Jutrczenka

አብዛኛው የጀርመን ሕዝብ ስደተኞቹን አስታኮ የመጣውን ችግር „…እንፈተዋለን“ የሚለውን ነገር ሙሉ በሙሉ አምኖ በልቡ አልተቀበለውም፡፡ በሌላ በኩል ጥናቶች እንደሚያሳዩት አሁንም ቢሆን ሥልጣን ላይ ተመርጠው በተቀመጡት የክርስቲያን ዲሞክራቶቹና በእህት ድርጅት፣ በክርስቲያን ሶሻል ዩኒየን ፓርቲ ላይ፣ መራጩ ሕዝብ፣ ለእነሱ የሚያሳየውን ድግፉን አሁንም ለእነሱ ከመስጠት ወደ ሁዋላ አላለም፡፡አሁንም ቢሆን ድርጅቱ ጠንካራ ድጋፍ በሕዝቡ ውስጥ አለው፡፡

በውጭ ጉዳይ ፖለቲካ ፖሊሲአቸውም ሆነ በሚያቀርቡት አመለካከታቸው መራሂተ መንግስትዋ እንደ አለፉት ዘመናት ዘንድሮም ፣ በአዉሮጳ መሪዎች ዘንድ ትልቅ ድምጽና ተቀባይነት አላቸው፡፡

በስደተኞች ጥያቄ ላይ ወይዘሮ አንጌላ ሜርክል የወሰዱትን እርምጃ አብዛኛው የአዉሮጳ አንድነት አባል አገሮች ባይደግፉትም ፣በሌሎች አንገብጋቢ የአዉሮጳ ጉዳዮች ላይ - እዚህ ላይ የብርታኒያንን አዉሮጳን ጥሎ መውጣት መመልከት ብቻ ይበቃል- መራሂተ መንግሥትዋየሚወስዱት አቋሞችና የሚያራምዱት ፖለቲካቸው፣ውሳኔአቸውም በአህጉሩ ውስጥ ፣አሁንም ፣ ትልቅ ቦታና ከፍተኛ ክብደት አለው፡፡

ስደተኞችን አስመልክተው የወሰዱትን ሰበአዊ ውሳኔአቸውን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሚስተር ባራክ ኦባማ ብቻ አይደሉም„… ጀርመን በዚህ እርምጃዋ ከታሪክ ጎን ቆማ ተገቢውን ቦታ ትይዛለች“ ብለው ያኔ ያለፈው ዓመት፣እሳቸው መራሂተ መንግስትዋን በውሳኔአቸውን ያደነቁት፡፡ ሌሎቹም በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦችም ጀርመን ቃሉዋን አክብራ ለአደጋ የተጋለጡትን ስደተኞችን በመቀበሉዋም እርምጃውን እነሱም አብረው ተገርመው አድንቀው ተቀብለውታል፡፡

ግን ያም ሁኖ ፣ ጀርመኖችም በስደተኞች ላይ ያላቸውና የነበራቸው አመለካከት ደግሞ እንዳለ ተቀይሮአል፡፡በመጀመሪያ ቀናት ይታይ የነበረው የእንግዳ ተቀባይነትና የማስተናገድ መንፈስ ቀስ እያለ እየቀዘቀዘና እየበረደ አሁን ሌላ መልክ ይዞአል፡፡

በዘመን መለወጫ ዋዜማ ላይ የታየው የአንዳንድ ስደተኛ ወንዶች ልጆች በጀርመን ኮረዳ ልጆች ላይ ያሳዩት አጸያፊ ድርጊት፣… ከእስላማዊ መንግሥት ሽብር ፈጣሪዎች ጋር የተያያዘው ግዲያና የግድያ ሙከራ ፣ከእሱም ጋር በቅርቡ የታየው የቦንብ ፍንዳታም - ምንም እንኳን አንዳንዶቹ ቀደም ብለው ከ2015 ዓ.ም በፊት እ.አ.አ. እዚህ ቢመጡም- እነዚህ ሁሉ አንድ ላይ ተደማምረው የኑዋሪውንና የመጤዎቹን ግንኙነት አሻክረው አሁን የምናየው አሳዛኝ ሁኔታ ላይ ነገሩን አድርሶታል፡፡

አሁን እንደምናውቀውና እንደተደረሰበት ደግሞ፣ የስደተኞች ነፍስ ለማዳን የተከፈተውን ዕድል፣ አክራሪ ሽብር ፈጣሪ እስላሞች ተጠቅመው፣ ድንበር አቋርጠው ወደ ጀርመን አገር ዘልቀው ለመግባት ችለዋል፡፡ ድንበሩ ቢዘጋ ደግሞ በሺህና በአሥር ሺህ ፣በመቶና በሁለት መቶ ሺህ የሚቆጠሩ ነፍሳቸውን ለማዳን የሚሸሹትን ስደተኞች መርዳት በአልተቻለ ነበር፡፡

ወጣ ወረደ ፤ ነገ ምን ይመጣል የሚለው ፍርሃቻውም እንዳለ ሁኖ ጀርመኖች ከአለፈው ዓመት ጀምሮ በተቻላቸው መጠን ስደተኞችን፣አሁንም ከመርዳት ወደሁዋላ አላሉም፣ አላቋረጡም ፡፡ ትናንሽ ልጆችን የጀርመንኛ ቋንቋ በማስተማር አንዴ የጀመሩትን ሥራ አሁንም ቀጥለውበት ያስተምሩአቸዋል፡፡ብቻቸውን እዚህ የደረሱትን ገና ለአቅመ አዳም ያልደረሱትን ወጣት ልጆች ወስደው እየተንከባከቡአቸው አሁንም ያሳድጉአቸዋል፡፡መሥራት ለሚፈልጉት ሥራ፣የሙያ ትምህርት ቤት ገብተው ለመማር ለሚፈልጉት ለእነሱም ትምህርት ቤት አብረው ፈልገው እዚያ ይልኩአቸዋል፡፡

በአጭሩ፡- አለ ወዶ ዘማቾች …በነጻ ምንም ገንዘብ ሳይጠይቁ ፣በሺህና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የጀርመን ተወላጆች፣ እዚህ በአንዴ ተነስተው ባይሰማሩ ኑሮ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ፣እዚህ የደረሱትን ስደተኞች በምንም ዓይነት በዚያን አጭር ጊዜ ውስጥ እነሱን መርዳት በጣም ከባድ ነበር፣ እንዲያውም አይቻልም ነበር፡፡

Deutschland Bus mit Flüchtlingen aus Landshut vor Kanzleramt Berlin
ምስል Getty Images/AFP/J. MacDougall

ማደሪያ ቦታ ለስደተኞች ማዘጋጀት ሌላው አስቸጋሪ ጉዳይ ነበር፡፡በሚሊዮን ከሚቆጠሩት አንዱም ስድተኛ መንገድ ላይ ሳያድር ሁሉንም ማስተናገድ በቀላሉ ታይቶ የሚታለፍ ሥራም አይደለም፡፡ የሆነው ሆኖ ፣አሁንም ቢሆን ትልቁ ገና ያልተፈታው ችግርም ከፊታችን ተደቅኖ እንደ ቆመም መረሣት የለብንም፡፡ እሱም ሕብረተሰቡ፣ የተገን ጠያቂን ስደተኛ ልጆችን፣ ትምህርት ቤት አስገብቶ እነሱን ማስተማር አለበት፡፡ነፍስ ያወቁትን ጎልማሦዎችን እንደዚሁ፣እነሱን አስተምሮና አሠልጥኖ የሥራ ዓለም ውስጥ ማሰማራትም ይኖርበታል፡፡

ይህ ሁሉ ደግሞ ሲሆን፣ ጊዜና ጉልበት፣ከዚያም በላይ ብዙ ወጪ ገንዘብም የሚጠይቅ፣ሥራና ኃላፊነት ነው፡፡ በዚያውም ላይ ይህ እርምጃ „ቅናትንና እኛ ተረሣን“ የሚለውን ጥያቄ በሕዝቡ መካከል አስነስቶ፣ የማያስፈልግ ክርክርና ግጭትን ፣አስነስቶ፣እሱንም ጋብዞ፣ የአገር ጸጥታንም፣ማን ያውቃል፣ወደፊት ይህ ጉዳይ ሊያደፍርስም ይችላል፡፡

በሌላ በኩል ይህ የስደተኞች ጥያቄና ፣እነሱን አስታኮ የተነሳው ጉዳይ -ማን ያውቃል ተረስቶ የነበረውን በእሴትና በተለያዩ እሴቶች ላይ ተመሥርቶ የተገነባውን የጀርመንን የጋራ ቤት፣ እንደገና ነፍስ ዘርቶ እኛ ማን ነን ብሎ ሰው እራሱ እራሱን ጠይቆ እንዲነጋገርበትም ፣የሕብረተሰቡ ክፍሎች፣እንዲወያዩበትም፣በጉዳዩ ላይ እንዲያስቡበት አዲስ መድረክ፣ሊከፍት ይችላል፡፡

እዚህ ቀርተው ለመኖር ለሚፈልጉ ስደተኞች ፣የጀርመንን ቋንቋ መማር፣ አላባቸው፡፡ሕብረተሰቡ የተመሠረተበተን እና የተገነባበትን ነጻና ዲሞክራቲክ የሆነውን እሴቶቹን መቀበል ወሳኝ እንደሆነ፣… አገሪቱም የምትተዳደርበት ሕገ-መንግሥቱም፣ ከመጽሐፍ ቅዱስና፣ከቅዱስ ቁራን ወይም ደግሞ ከማንኛውም የሐዋሪያት ሥራ በላይ ሁኖ ሁሉንም ፣ወንዱንም ሴቱንም እኩል የሚያስተናግድ መመሪያ እንደሆነ መቀበልን፣ከእነሱ ይጠይቃል። ሕግን የማያከብሩ፣ይህን የጋራ የሆነውን ሕግን የሚጥሱ ፣በወንጄል ሥራ የተሠማሩ የውጭ አገር ሰዎችን ደግሞ፣ እንደ ሥራቸውና እንደ ጥፋታቸው ፣በአስቸኳይ ጀርመንን ለቀው እንዲወጡም ይደረጋል፡፡ አዎን …ምን ይደረጋል ! የስደተኞች ጉዳይና እነሱ ይዘውት የመጡት ያልተሰበ ቀውስ፣አሁን ጀርመኖችን፣ ተዝናንተው በሰላም ከሚኖሩበት የሞቀ ቤታቸው ተነስተው ምን ማደረግ እንደአለባቸው የሚወዘውዛቸው ጥያቄ ሁኖአዋል፡፡

Berlin Kanzleramt Flüchtlingsgipfel
ምስል picture-alliance/dpa/B. von Jutrczenka

ይህ አዲስ ሁኔታ ደግሞ አዲስ ነገር ይዞልን ሊመጣም ይችላል፡፡ ጥሩው ዜና እዚህ ላይ ፣ከተለያዩ ባህልና የሥልጣኔ ዓለም የመጡ ስደተኞች የጀርመንን ባህል እንደገና አሳምረውትና አሳድገውት ሌላ መልክ ሰጥተውት የበለጠ ደረጃ ላይ ያደርሱታል፡፡ ቁም ነገሩ ያለው ስደተኞቹን አቅፎና ተቀብሎ እነሱን ከሕብረተሰቡ ጋር በቀላሉ እንዲዋሃዱ መርዳቱ ላይ ነው፡፡ ያኔ ነው አብረው እነሱም ጀርመንን በአላቸው ችሎታ ለመገንባት አስተዋጽኦቸውን የሚያበረክቱት፡፡

አገራቸውንም ሊረዱ ይችላሉ፡፡ እንደሚታወቀው የጀርመን መንግሥት ለዕድገትና ለልማት በየዓመቱ ወጪ ከሚያደርገው የበለጠ ፣ ወደዚያ የሚልኩት ሐብትና ገንዘብ እጅግ የላቀ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ጀርመኖች፣ እዚህ የደረሱትን ስደተኞች እንደ አንዳች መዓትና እንደ ችግር ሳይዩ የእነሱን መምጣት በጥሩ መንፈስ ተርጉመው ከተመለከቱትና ፣በደንብ በሥነ-ሥርዓቱ ከተገነዘቡት ፣የሁዋላ ሁዋላ ይህ በሰዎች መካከል -ያውም በመከራ ዘመን የሚደረገው ሰበአዊ ዕርዳታ፣ ትብብርና ሕብረት በመጨረሻው እንዳች ፍሬ ስጥቶ ፣የተደረገው ድካም ግሩም ነው ብለን የምናደንቅበት ጊዜ ይመጣል፡፡ በዚህ አኳይ ደግሞ የጀርመን ሕብረተስብ ከተቀየረ እጅግ ደስ ያሳኛል፡፡

ቬሪቻ ስፓሶቭስካ/ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አዜብ ታደሰ